ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፮፥፲፬። ከማቴዎስ ፮፥፲፫ ጋር አነጻፅሩ፤ በሉቃስ ፲፩፥፬ም እንደዚህ አይነት ቅያሬዎች ነበሩ
ጌታ ወደ ፈተና አይመራንም።
፲፬ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና ለመግባት እንዳንመራ አትፍቀድልን።
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፮፥፳፪። ከማቴዎስ ፮፥፳፪ ጋር አነጻፅሩ
አይኖቻችን ለእግዚአብሔር ክብር የቀኑ ከሆኑ፣ ሰውነቶቻችን በሙሉ በብርሀን ይሞላሉ።
፳፪ የሰውነት መብራት ዓይን ናት፤ ዓይንህ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ክብር የቀናች ብትሆን፣ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል።
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፮፥፳፭–፳፯። ከማቴዎስ ፮፥፳፭፤ ፲፥፲ ጋር አነጻፅሩ
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለስራቸው አስቸጋሪነት አስጠነቀቃቸው ነገር ግን መንገድን እንደሚያዘጋጅላቸው እና የሰማይ አባት እንደሚሰጣቸው ቃል ገባ።
፳፭ እንደገናም እላችኋለሁ፥ ወደ አለም ሂዱ፣ እናም ስለአለም አታስቡ፤ ምክንያቱም አለም ይጠላችኋል፣ እናም ይሰድዳችኋል፣ እናም ከምኩራባችሁ ያስወጧችኋል።
፳፮ ይህም ቢሆን፣ ህዝብን በማስተማር ከቤት ወደቤት ትሄዳላችሁ፤ እኔም በፊታችሁ እሄዳለሁ።
፳፯ እናም የሰማይ አባትችሁ ለምግብ ምንም የሚያስፈልጋችሁን፣ ምን እንደምትበሉ ይሰጣችኋል፤ እና ለመሸፈኛም፣ የምትለብሱትንም።
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፮፥፴፰። ከማቴዎስ ፮፥፴፫ ጋር አነጻፅሩ
መጀመሪያ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት መፈለግ ይገባናል።
፴፰ ስለዚህ፣ የዚህን አለም ነገሮች አትፈልጉ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመገንባት፣ እና ጽድቁንም ለመመስረት ፈልጉ፣ እና እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይጨመርላችኋል።