የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፩፣ ፭–፮፣ ፰–፱።ማቴዎስ ፬፥፩፣ ፭–፮፣ ፰–፱ ጋር አነጻፅሩ፤ በሉቃስ ፬፥፪፣ ፭–፲፩ም እንደዚህ አይነት ቅያሬዎች ነበሩ

ኢየሱስ የተመራው በመንፈስ እንጂ በሰይጣን አይደለም።

ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ይሆን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረበዳ ወሰደው።

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅድስት ከተማ ተወሰደ፣ እና መንፈስ እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቆመው።

ከእዚያም በኋላ ዲያብሎስ ወደእርሱ መጣ እና እንዲህ አለው፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፣ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።

ደግሞም፣ ኢየሱስ በመንፈስ ውስጥ ነበር፣ እና ይህም ወደ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፣ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳየው።

እና ዲያብሎስም ወደ እርሱ እንደገና መጣ፣ እና አለው፣ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፲፩።ማቴዎስ ፬፥፲፩ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስን ለማገልገል መላእክት ላከ።

፲፩ አሁንም ኢየሱስ ዮሐንስ ወደ እስር ቤት እንደተጣለ አወቀ፣ እና እርሱም መላእክትን ላከ፣ እና እነሆ፣ እነርሱም መጡና አገለገሉት።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፲፰።ማቴዎስ ፬፥፲፱ ጋር አነጻፅሩ

ብሉይ ኪዳን ነብያት ስለኢየሱስ ይናገራሉ።

፲፰ እርሱም በነብያት የተጻፈለት እኔ ነኝ፤ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፬፥፳፪።ማቴዎስ ፬፥፳፫ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ በስሙ ካመኑት መካከል ህዝቦችን ፈወሰ።

፳፪ ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በስሙ በሚያምኑት ሕዝብም መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።