የጥናት እርዳታዎች
ጳውሎስ


ጳውሎስ

በአዲስ ኪዳን ውስጥ የነበረ ሐዋሪያ። የጳውሎስ እብራውያን ስም ሳዖል ነበር፣ እናም ወደ አህዛብ ተልዕኮውን እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ በዚህ ስም ይታወቅ ነበር። ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያኗን ያሳድድ ነበር ነገር ግን የኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይን ካየ በኋላ ወደ እውነቱ ተቀይሮ ነበር። ጳውሎስ በሶስት ታላቅ የሚስዮን ጉዞዎች ሄደ እናም ብዙ ደብዳቤዎችን ለቅዱሳን ጻፈ። ከእነዚህ ደብዳቤዎች መካከል አስራ አራቱ ዛሬ የአዲስ ኪዳን ክፍል ናቸው። በመጨረሻው ወደ ሮሜ እንደ እስረኛ ተወስዶ ነበር እናም ምናልባት በጸደይ በ፷፭ ዓ.ም. ውስጥ ተገደለ።