የልሳኖች ስጦታ ደግሞም ምላስ; የመንፈስ ስጦታዎች ተመልከቱ የተነሳሱ ሰዎች የማያውቁትን ቋንቋ ለመናገር፣ ለማስተዋል፣ እና ለመተርጎም የሚያስችላቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ። በልሳኖች ስጦታ እናምናለን (እ.አ. ፩፥፯)። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር, የሐዋ. ፪፥፬. በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም, ፩ ቆሮ. ፲፬፥፩–፭፣ ፳፯–፳፰. በልሳኖች መናገር ለማያምኑ ምልክት ነው, ፩ ቆሮ. ፲፬፥፳፪–፳፰. ከዚያም የእሳትና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይመጣል፤ እናም ከዚያ በኋላ በመላዕክት ልሳን መናገር ትችላላችሁ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፲፫–፲፬. አማሌቂ ሁሉም ሰዎች በልሳኖች መናገርን እንዲያምኑ አበረታታ, ኦምኒ ፩፥፳፭. ለአንዳንዶቹ በልሳን መናገር ተሰጥቷቸዋል፣ ለሌላም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ተሰጥቷቸዋል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፳፬–፳፭ (፩ ቆሮ. ፲፪፥፲; ሞሮኒ ፲፥፰፣ ፲፭–፲፮). የልሳኖች ስጦታ በህዝቦችህ ላይ ይፍሰስ, ት. እና ቃ. ፻፱፥፴፮.