የጥናት እርዳታዎች
ዮሐንስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ


ዮሐንስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከነበሩት አስራ ሁለት ሐዋሪያት አንዱ፣ የዘብዴዎስ ልጅ፣ እና የያዕቆብ ወንድም። በመጀመሪያው ህይወቱ አሳ አጥማጅ ነበር (ማር. ፩፥፲፯–፳)። ምናልባት በዮሐ. ፩፥፵ ውስጥ የተጠቀሰው ስሙ ያልተነገረው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ነው። በኋላም የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዲሆን ጥሪ ተቀበለ (ማቴ. ፬፥፳፩–፳፪ሉቃ. ፭፥፩–፲፩)። የዮሐንስ ወንጌልን፣ ሶስት መልእክቶችን፣ እና የዮሐንስ ራዕይን ፅፏል። የኢያኢሮስ ሴት ልጅ ከሞት በተነሳችበት ጊዜ (ማር. ፭፥፴፭–፵፪)፣ በመለወጫ ተራራ ላይ (ማቴ. ፲፯፥፩–፱)፣ እና በጌቴሴማኒ ውስጥ (ማቴ. ፳፮፥፴፮–፵፮) ከጌታ ጋር ከነበሩት ሶስቱ አንዱ ነበር። በፅሁፉም ውስጥ ስለራሱ በኢየሱስ እንደተወደደ ደቀ መዛሙርት (ዮሐ. ፲፫፥፳፫፳፩፥፳) እና እንደ “ሌላው ደቀ መዛሙርት” (ዮሐ. ፳፥፪–፰) ተናግሯል። ኢየሱስ እርሱንና ወንድሙን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው (ማር. ፫፥፲፯)። በስቅለት እና ትንሳኤ ታሪክ ውስጥ እርሱ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል (ሉቃ. ፳፪፥፰ዮሐ. ፲፰፥፲፭፲፱፥፳፮–፳፯፳፥፪–፰፳፩፥፩–፪)። ዮሐንስ ወደ ፍጥሞ ተወገደ፣ በእዚያም የዮሐንስ ራዕይን ጻፈ (ራዕ. ፩፥፱)።

በኋለኛው ቀን ራዕይ ውስጥም ዮሐንስ ተደጋግሞ ተጠቅሷል (፩ ኔፊ ፲፬፥፲፰–፳፯፫ ኔፊ ፳፰፥፮ኤተር ፬፥፲፮ት. እና ቃ. ፯፳፯፥፲፪፷፩፥፲፬፸፯፹፰፥፻፵፩)። እነዚህ ምንባቦች የዮሐንስን የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገብን ያረጋግጣል እናም ስለእርሱ ታላቅነት እና በብሉይ ኪዳን ዘመናት እና በመጨረሻው ቀናት በምድር ላይ እንዲያከናውን ጌታ ስለሰጠው ስራ አስፈላጊነት አስተያየት ይሰጣሉ። የኋለኛው ቀን ቅዱሣት መጻህፍት ዮሐንስ እንዳልሞተ ነገር ግን እስከ ጌታ ዳግም ምፅዓት ድረስ በምድር እንደአገልጋይ እንዲቆይ እንደተፈቀደለት ግልፅ ያደርጋሉ (ዮሐ. ፳፩፥፳–፳፫፫ ኔፊ ፳፰፥፮–፯ት. እና ቃ. ፯)።

የዮሐንስ መልእክቶች

ምንም እንኳን የእነዚህ ሶስት መልእክቶች ጸሀፊ እራሱን በስም ባይጠቅስም፣ ቋንቋው የሐዋሪያው ዮሐንስ ፅሁፍ ጋር በጣም የተመሳሰሉ ስለሆኑ እርሱ ሶስቱንም እንደጻፋቸው ይገመታል።

፩ ዮሐንስ ፩ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ጋር ጓደኝነትን እንዲያገኙ ይገስጻል። ምዕራፍ ፪ ቅዱሳን እግዚአብሔርን በታዛዥነት እንዲያውቁት ትኩረት ይሰጣል እናም አለምን እንዳያፈቅሩ ያስተምራል። ምዕራፍ ፫ ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ እና እርስ በራስ እንዲዋደዱ ጥሪ ይሰጣል። ምዕራፍ ፬ እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ እና በሚያፈቅሩት ውስጥ እንደሚኖር ይገልጻል። ምዕራፍ ፭ ቅዱሳን በክርስቶስ እምነት በኩል በእግዚአብሔር እንደተወለዱ ይገልጻል።

፪ ዮሐንስ ከ፩ ዮሐንስ ጋር አንድ አይነት ነው። በእዚህም “በምርጥ ሴቷ” ልጆች ታማኝነት ምክንያት ተደሰተ።

፫ ዮሐንስ ጋይዮስ የሚባልን ሰው ለታማኝነቱ እና እውነቱን ለሚያፈቅሩት ለሰጠው እርዳታ ያሞግሳል።

የዮሐንስ ወንጌል

በእዚህ የአዲስ ኪዳን መፅሐፍ ውስጥ፣ ሐዋሪያው ዮሐንስ (፩) ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ወይም መሲህ እንደሆነ እና (፪) ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መሰከረ (ዮሐ. ፳፥፴፩)። የሚገልጻቸው የኢየሱስ ህይወቶች በጥንቃቄ የተመረጡ ናቸው እናም በዚህ አላማም የተዘጋጁ ነበሩ። መፅሐፉ የሚጀምረው ክርስቶስ በቅድመ ምድር ህይወት ስለነበረው ስልጣን መግለጫ ነው፥ እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፣ እርሱም እግዚአብሔር ነበር፣ እናም እርሱ የሁሉም ነገሮች ፈጣሪ ነበር። በስጋ እንደ አብ አንድያ ልጅ የተወለደ ነበር። ዮሐንስ የእርሱን መለኮታዊነት እና ከሞት መነሳቱን ታላቅ አፅንዖት በመስጠት የኢየሱስ አገልግሎት መንገድን ይከታተላል። ኢየሱስ በተአምራት፣ በምስክሮች፣ በነቢያት፣ እና በክርስቶስ በእራሱ ድምፅ እንደተመሰከረው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በግልፅ ያረጋግጣል። ዮሐንስ ብርሀንንና ጨለማን፣ እውነትንና ስህተትን፣ ጥሩንና ክፉን፣ እግዚአብሔርንና ዲያብሎስን በማነጻጸር ያስተምራል። ምናልባት ስለኢየሱስ ቅዱስነት እና ስለአይሁድ መሪዎች እምነተ ቢስነት በግልፅ የሚገልፅ ሌላ ምንም መዝገብ የለም።

ዮሐንስ ስለክርስቶስ የይሁዳ አገልግሎት፣ በልዩም ስለስጋዊ አገልግሎቱ የመጨረሻ ሳምንት፣ ሲፅፍ፣ ዋና ጽሁፋቸው ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ እና ሉቃስ ስለገሊላ አገልግሎቱ ነበር። ከዚህ ወንጌል ብዙዎቹ በኋለኛው ቀን ራዕይ ተገልጸዋል (ት. እና ቃ. ፯ እና ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፴፰–፻፵፩)።

በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የተገለጹትን የአዳኝ ህይወት ድርጊቶችዝርዝር፣ የወንጌሎች ስምምነትን ተመልከቱ።

ለራዕይ መፅሐፍ