ክፍል ፵፬
በየካቲት መጨረሻ አካባቢ፣ በ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ውስጥ የቀረቡትን ትእዛዛት በማክበር፣ ቤተክርስቲያኗ በሚቀጥለው ሰኔ መጀመሪያ ላይ ጉባኤ እንዲኖር መደበች።
፩–፫፣ ሽማግሌዎች በጉባኤ ይሰብሰቡ፤ ፬–፮፣ በምድሪቷ ህግጋት መሰረት እናም ደሆችንም ይንከባከቡ ዘንድ ራሳቸውን ያደራጁ።
፩ እነሆ፣ ጌታ ለእናንተ ለአገልጋዮቼ እንዲህ ይላል፣ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ከምስራቅና ከምእራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ በደብዳቤ ወይም በሌላ መንገድ፣ መሰብሰባቸው ፍቃዴ ነው።
፪ እናም እንዲህ ይሆናል ያልፋል፣ ታማኝ ቢሆኑ፣ እና በእኔም ያላቸውን እምነት ቢጠቀሙ፣ ራሳቸውን በሚሰበስቡበት ቀን ሀመንፈሴን አፈስባቸዋለሁ።
፫ እናም እንዲህ ይሆናል በአካባቢው ክፍለ ሀገሮች ይሂዱ፣ እና ለህዝቡ ንስሀን መግባትን ሀይስበኩ።
፬ እና፤ እንዲህም ሆኖ ሀበሰው ህግጋት መሰረት ራሳችሁን ለማደራጀት ሀይልን እስካገኛችሁ ድረስ ብዙዎች ለይለወጣሉ፤
፭ ሀጠላቶቻችሁ በእናንተ ላይ ስልጣን እንዳይኖራቸው በሁሉም ነገሮች እንድትጠበቁ፣ ህግጋቴንም ለመጠበቅ እንድትችሉ፣ ጠላትም ህዝቤን ለማጥፋት የሚሻባቸው ስምምነቶች ይሰበሩ ዘንድ ራሳችሁን ለማደራጀት ሀይል ታገኛላችሁ።
፮ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ሁሉም ነገሮች በተቀበላችሁት ህጌ መሰረት እስከሚከናወኑ ድረስ ይጠበቁ ዘንድ፣ ደሆችንና ችግረኞችን ሀተንከባከቡ እና በሚያስፈልጋቸውም ነገሮች አገልግሏቸው። አሜን።