ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷


ክፍል ፷

በነሀሴ ፰፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በጃክሰን አውራጃ ሚዙሪ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ ወደ ጃክሰን አውራጃ የተጓዙ እና በመሬቱና በቤተመቅደስ መገንቢያ ቦታ መቀደስ የተሳተፉ ሽማግሌዎች ምን ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ለማወቅ ፈልገው ነበር።

፩–፱፣ ሽማግሌዎች በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል ወንጌልን ይስበኩ፤ ፲–፲፬፣ ጊዜአቸውን አያጠፉም እናም ችሎታቸውንም አይደብቁም፤ ፲፭–፲፯፣ ወንጌሉን ባልተቀበሉት ላይ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እግራቸውን ይጠቡ።

እነሆ፣ ወደመጡበት አገር ፈጥነው ለሚመለሱት ለቤተክርስቲያኑ ሽማግሌዎች ጌታ እንዲህ ይላል፥ እነሆ፣ ወደዚህ ስፍራ መምጣታችሁ አስደስቶኛል፤

ነገር ግን በአንዳንዶች አልተደሰትኩም፣ አንደበቶቻቸውን አልከፈቱምና፣ ነገር ግን ሰውን በመፍራት የሰጠኋቸውን ችሎታ ደብቀዋል። ለእነዚህ አይነቶችም ወዮላቸው፣ ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ነዳለችና።

እናም እንዲህ ይሆናል፣ ለእኔ ይበልጥ ታማኝ ካልሆኑ ይህም፣ እንዲሁም ያላቸውም፣ ይወሰድባቸዋል

እኔ ጌታ ከላይ በሰማያት፣ እናም በምድር ሰራዊት መካከልም እገዛለሁና፤ እናም እንቁዎቼን በምሰበስብበት ጊዜ፣ ሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ሀይልን የሚያውጀው ምን እንደሆነም ያውቃሉ።

ነገር ግን፣ ወደ መጣችሁበት አገር ስለምትጓዙበትም እነግራችኋለሁ። ለእኔ ምንም ልዩነት ስለሌለው፣ እንደሚመስላችሁ መዘውር ይሰራ ወይም ይገዛ፣ እናም ሴንት ሉዊስ ወደሚባለው ከተማም ፈጥናችሁ ተጓዙ።

ከዚያም ቦታ አገልጋዮቼ ስድኒ ሪግደን፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና ኦሊቨር ካውድሪ ም ወደ ስንሰናቲ ይጓዙ፤

እናም በዚህ ስፍራም ድምጻቸውን አንስተው፣ ያለ ቍጣና አለ ጥርጥር፣ ቅዱስ እጆችን በማንሳት፣ በጎላ ድምፅ ቃላቴን ይግለጹ። ቅዱሳን አደርጋችሁ ዘንድ ይቻለኛልና፣ እናም ኃጢአቶቻችሁም ተሰርየዋል

እና የሚቀሩትም፣ ከመጡባቸው ቤተክርስቲያኖች እስከሚመለሱ ድረስ፣ ሁለት በሁለት በመሆን፣ እናም በችኮላ ሳይሆን፣ ቃሉን በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል በመስበክ፣ ከሴንት ልዊስ ጎዞአቸውን ይጀምሩ።

እናም ይህም ሁሉ ለቤተክርስቲያኖቹ ጥቅም ነው፤ ለዚህም ምክንያት ልኬአቸዋለሁና።

እናም አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ የሰጠሁትን ገንዘብ፣ እንዲመለሱ ለታዘዙት ለእኔ ሽማግሌዎች ክፈሉን ይስጥ፤

፲፩ እና የሚችለውም፣ በወኪሉ በኩልም ይህን ይመልስ፤ እናም ከማይችለውም፣ ከእርሱ ይህ አይጠበቅበትም።

፲፪ እናም አሁን ወደዚህ ምድር እየመጡ ስላሉትም ቅሪቶች እናገራለሁ።

፲፫ እነሆ፣ በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል ወንጌሌን እንዲሰብኩ ተልከው ነበር፤ ስለዚህ፣ እንዲህም ትእዛዝ እሰጣቸዋለሁ፥ ጊዜአችሁን አታጥፉችሎታችሁንም እንዳይታወቁ አትቅበሩ።

፲፬ እናም ወደ ፅዮን ምድር ከመጣችሁም እናም ቃሌን ካወጃችሁ በኋላ፣ በችኮላ፣ ወይም በቁጣ ወይም በጥላቻ ሳይሆን፣ በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል ወንጌሌን በማወጅ ፈጥናችሁ ተመለሱ።

፲፭ እናም እንዳታስቆጧቸው በፊት ለፊታቸው ሳይሆን በሚስጥር፣ በማይቀበሏችሁም ላይ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ፤ ይህም በፍርድ ቀን ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እግራችሁን እጠቡ።

፲፮ እነሆ፣ ይህም ለእናንተ በቂ እናም የእርሱ የላካችሁም ፈቃድ ነው።

፲፯ እናም በአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ አንደበት በኩልም ስለስድኒ ሪግደን እና ኦሊቨር ካውድሪ ይገለጣል። የሚቀረውም ከዚህ በኋላ ይገለጣል። እንዲህም ይሁን። አሜን።