ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፪


ክፍል ፪

በመስከረም ፳፩፣ ፲፰፻፳፫ (እ.አ.አ.) ምሽት በማንችስተር፣ ኒው ዮርክ በነቢዩ አባት ቤት ውስጥ ከመልአኩ ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ከተሰጡ ቃላት ከጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ውስጥ የተውጣጣ ምንባብ። በአሁኑ ወቅት መፅሐፈ ሞርሞን በመባል በአለም ፊት ያለውን ጽሁፍ ከጻፉት ረጅም የታሪክ ጸሀፊያን ሀረግ ሞሮናይ የመጨረሻው ነበር (ሚልኪያስ ፬፥፭–፮፤ እንዲሁም ክፍሎች ፳፯፥፱፻፲፥፲፫–፲፮፤ እና ፻፳፰፥፲፰ን አነጻጽሩ።)

፣ ኤሊያስ ክህነትን ይገልጣል፤ ፪–፫፣ የአባቶች የተስፋ ቃል በልጆች ልብ ይተከላል።

እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት በነቢዩ ኤሊያስ እጅ ክህነትን እገልጥላችኋለው።

እናም ለአባቶች የተገባውን የተስፋ ቃል በልጆች ልብ ይተክላል፣ እናም የልጆቹም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመለሳል።

እንዲህ ባይሆን ኖሮ፣ መላው ምድር በምጽአቱ በጠፋ ነበር።