ክፍል ፲፩
ግንቦት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለወንድሙ ለሀይረም ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ይህም ራዕይ የተሰጠው በኡሪም እና ቱሚም አማካይነት ለጆሴፍ ልመናና ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነበር። ይህ ራዕይ የአሮናዊ ክህነት ዳግመኛ ከተመለሰ በኋላ መሰጠቱን የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ያሳስባል።
፩–፮፣ በወይኑ ስፍራ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ደህንነትን ያገኛሉ፤ ፯–፲፬፣ ጥበብን እሹ፣ ንስሐን አውጁ፣ በመንፈስ ታመኑ፤ ፲፭–፳፪፣ ትዕዛዛቱን ጠብቁ፣ እናም የጌታን ቃል አጥኑ፤ ፳፫–፳፯፣ የራዕይን እናም የትንቢትን መንፈስን አትካዱ፤ ፳፰–፴፣ ክርስቶስን የሚቀበሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ።
፩ በሰዎች ልጆች መካከል ታላቅ እና ሀድንቅ ስራ ሊመጣ ነው።
፪ እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ፈጣን እና ሀሀያል፣ ሁለት አንደበት ካለው ሰይፍ ይልቅ ለየተሳለ፣ መገጣጠሚያን እና መቅኔን የሚለየውን ሐቃሌን መአድምጥ፤ ስለዚህ ቃሌን እድምጥ።
፫ እነሆ፣ የእርሻው ስፍራ ሀነጭ ሆኖ አዝመራው ዝግጁ ነው፤ ስለዚህ፣ መሰብሰብ የሚሻ ሁሉ ኃይሉ ይጨድ፣ እናም ለነፍሱም ለዘለአለማዊ ደህንነት በእግዚአብሔር መንግስት ሐያከማች ዘንድ ቀን ሳለ ይሰብስብ።
፬ አዎን፣ ማንኛውም ሀየሚያጭድ እናም የሚሰበስብ ሁሉ እንዲሁ በእግዚአብሔር የተጠራ ነው።
፭ ስለዚህ፣ እኔን ሀከጠየቅህ ትቀበላለህ፤ ካንኳኳህ ይከፈትልሀል።
፮ አሁን፣ እንደጠየቅኸው፣ እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ ትእዛዛቴን ጠብቅ እናም ሀየፅዮንን አስተሳሰብ ለማምጣት እና ለመመስረት ፈልግ፤
፯ ሀጥበብን እንጂ ለባለጠግነትን አትሻ፤ እናም፣ እነሆ፣ የእግዚአብሔር ሚስጥራት ይገለጡልሀል፣ እናም ባለጠጋም ትሆናለህ። እነሆ፣ ዘለዓለማዊ ሕይወት ያለው ሰው ባለጠጋ ነው።
፰ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ላደርግልህ እንደምትሻው እንዲሁ ይደረግልሀል፤ እናም፣ ፈቃድህም ከሆነ፣ በዚህ ትውልድ ውስጥ የብዙ መልካም ስራ መከናወን መንስኤ ትሆናለህ።
፱ ለዚህ ትውልድ ሀከንስሀ በቀር ሌላ ምንም ለአትናገር፤ ትእዛዛቴን ጠብቅ፣ እናም ስራዬን በትእዛዜ ሐመሰረት እንዲከናወን እርዳ፣ እናም ትባረካለህ።
፲ እነሆ፣ ሀስጦታ አለህ፣ ወይም በእምነት፣ ለበታመነ ልብ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይል፣ ወይም አንተን በሚናገርህ ሀይሌ በማመን ከእኔ ከፈለግህ ስጦታ ይኖርሀል፤
፲፩ ስለሆነም፣ እነሆ፣ የምናገረው እኔ ነኝ፣ በጭለማ የማበራው ሀብርሀን እኔ ነኝ፣ እናም ለአንተ እነዚህን ቃላት ለበሀይሌ እሰጥሀለሁ።
፲፪ እናም አሁን፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ወደ መልካም፣ አዎን፣ በትክክል ለመስራት፣ ሀበትህትና ለለመራመድ፣ በጽድቅ ሐለመፍረድ፣ በሚመራው መመንፈስ ላይ ሠእምነትህን አድርግ፤ እና መንፈሴም ይህ ነው።
፲፫ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ከመንፈሴ ሀአእምሮህን ለእንዲያበራ፣ ነፍስህን ሐበደስታ እንዲሞላ እሰጥሀለሁ፤
፲፬ እናም ከዚያም ታውቃለህ፣ ወይም ሀየጽድቅን ነገሮች በተመለከተ ከእኔ የምትሻቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ በእምነት በእኔ በማመን እንደምትቀበል በዚህ ታውቃለህ።
፲፭ እነሆ፣ እስከምትጠራ ድረስ ለመስበክ ሀእንደተጠራህ አድርገህ ማሰብ እንደሌለብህ አዝሀለሁ።
፲፮ የትምህርቴን እርግጠኝነት ታውቅ ዘንድ ቃሌን፣ ሀአለቴን፣ ቤተክርስቲያኔን እናም ወንጌሌን እስክትቀበል ድረስ፣ ለጥቂት ጊዜ ጠብቅ።
፲፯ እናም ከዚያም፣ እነሆ እንደመሻትህ፣ አዎን፣ እንደ እምነትህም እንዲሁ ይደረግልሀል።
፲፰ ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ ዝም በል፤ ለመንፈሴ መቃቀትን አድርግ፤
፲፱ አዎን፣ የተነገሩትን ነገሮች ወደብርሀን በማምጣት ትረዳ ዘንድ፣ በሙሉ ልብህ ወደ እኔ ሀጽና—አዎን፣ የስራዬን ትርጉም፤ እስከምታጠናቅቅም ድረስ ትዕግስተኛ ሁን።
፳ እነሆ፣ አዎን፣ በሙሉ ሀይልህ፣ አዕምሮህ እናም ጉልበትህ፣ ትእዛዛቴን ሀመጠበቅ ይህ የአንተ ስራ ነው።
፳፩ ቃሌን ለማወጅ አትፈልግ፣ ነገር ግን አስቀድመህ ቃሌን ሀለማግኘት ፈልግ፣ እናም ከእዚያ አንደበትህ ይፈታል፤ ከዚያም፣ ፈቃድህ ከሆነ፣ አዎን፣ ሰዎችን ለማሳመን የእግዚአብሔር ሀይል የሆነውን ቃሌን እና መንፈሴን ትቀበላለህ።
፳፪ ነገር ግን አሁን ዝም በል፤ አዎን፣ በዚህ ትውልድ ለሰው ልጆች ሀየምሰጠውን እስክትቀበል ድረስ፣ በሰዎች መካከል የሄደውን ለቃሌን ሐአጥና እናም ደግሞም በሰዎች መካከል የሚመጣውን መቃሌን፣ ወይም አሁን እየተተረጎመ ያለውን አጥና፣ እናም ሁሉም ነገሮች በዚያ ላይ ይጨመራሉ።
፳፫ እነሆ አንተ ልጄ ሀሀይረም ነህ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ለፈልግ፣ እናም እንደ ፅድቅ መሰረት ሁሉም ነገሮች ይጨመራሉ።
፳፭ ሀየራዕይ መንፈስንም ሆነ፣ ለየትንቢትን መንፈስ አትካድ፣ ይህንን ለሚክድ ለእርሱ ወዮለት፤
፳፮ ስለዚህ፣ በእኔ ጥበብ እስክትወጣ ድረስ በልብህ ቃሌን ሀአከማች።
፳፯ እነሆ፣ መልካም ፈቃድ ላላቸው፣ እናም ሀበማጭዳቸው ለመሰብሰብ ለሚያጭዱ ሁሉ እናገራለሁ።
፳፰ እነሆ፣ እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ሀኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። እኔ የአለም ህይወት እና ለብርሀን ነኝ።
፳፱ የእኔም ወደሆኑት መጥቼ የእኔም ያልተቀበሉኝ እኔው ራሴው ነኝ፤
፴ ነገር ግን እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ለተቀበሉኝ ሁሉ፣ በስሜ ለሚያምኑት እንኳን፣ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ሀልጆች ይሆኑ ዘንድ ለስልጣንን እሰጣቸዋለሁ። አሜን።