ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፮


ክፍል ፳፮

በሐምሌ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒያ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ለኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ለጆን ዊትመር የተሰጠ ራዕይ። (የክፍል ፳፬ ርዕስን ተመልከቱ)።

ቅዱሳን መጻህፍትን እንዲያጠኑ እና እንዲሰብኩ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ ፣ የጋራ ስምምነት ህግ ጸደቀ።

እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ ወደ ምዕራብ የሚቀጥለውን ጉባዔ ለማድረግ እስክትሄዱ ድረስ ጊዜአችሁን በቅዱሳን መጻህፍት ጥናት፣ ስብከት፣ በኮለስቪል ያለውን ቤተክርስቲያን በማጠንከር፣ በምድሩ ላይ ስራችሁን እንድታከናውኑ ይጠበቅባችኋል፣ እናም በመቀጠልም ምን እንደምታከናውኑ ይነገራችኋል።

እናም ሁሉም ነገሮች በቤተክርስቲያን በጋራ ስምምነት፣ በብዙ ጸሎት እና እምነት ይከናወናሉ፣ ሁሉንም ነገሮች በእምነት ትቀበላላችሁ። አሜን።