ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፴፬


ክፍል ፴፬

ህዳር ፬፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈያት፣ ኒው ዮርክ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለኦርሰን ፕራት የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ ወንድም ፕራት አስራ ዘጠኝ አመቱ ነበር። ከስድስት ሳምንት ቀደም ብሎ ከታላቅ ወንድሙ፣ ከፓርሊ ፒ ፕራት ዳግም ስለተመለሰው ወንጌል ስብከት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰማ ተለወጠና ተጠመቀ። ይህ ራዕይ የተሰጠው በፒተር ዊትመር ቀዳማዊ ቤት ውስጥ ነበር።

፩–፬፣ በእምነት የተሞሉት በኃጢአት ክፍያው አማካይነት የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ፤ ፭–፱፣ የወንጌል ስብከት የዳግም ምጽአትን መንገድ ያዘጋጃል፤ ፲–፲፪፣ ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ሀይል አማካይነት ይመጣል።

ልጄ ኦርሰን፣ እኔ ጌታ አምላክ፣ እናም እንዲሁም ቤዛህን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ የምንናገረውን ስማ እናም አድምጥ፣ እንዲሁም ተመልከት፤

በጭለማ የሚያበራ እና ጭለማም የማይረዳውን፣ እኔ የአለም ብርሀን እና ሕይወት የሆንኩትን፤

ያመኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ አለምን በመውደድ እርሱ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠውን ስማ እናም አድምጥ፣ እንዲሁም ተመልከት። ስለዚህም አንተ ልጄ ነህ፤

እናም በማመንህ ምክንያት የተባረክ ነህ፤

እናም ይበልጡን የተባረክ ነህ ምክንያቱም ወንጌሌን እንድትሰብክ በእኔ ተጠርተሀል

ለጠማማና ክፉ ትውልዶች፣ ለዳግም ምፅአቱ የጌታን መንገድ በማዘጋጀት ንስሀን ጩህ እናም ረጅም እና ጉልህ እንደሆነው መለከት ድምጽ ድምጽህን ከፍ አድርግ።

እነሆ፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ በኃይልና በታላቅ ክብር በደመና ውስጥ የምመጣበት ጊዜ ተቃርቧልና።

እናም ሁሉም ህዝብ ስለሚንቀጠቀጡ፣ የምጽአቴም ጊዜ ታላቅ ቀን ይሆናል።

ነገር ግን ያ ታላቁ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ጸሀይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ወደ ደምነት ትለወጣለች፤ እናም ከዋክብትም ብርሀናቸውን መስጠት ይከለክላሉ፣ አንዳንዶቹም ይወድቃሉ፣ እና ታላቅ ጥፋትም ኃጢአተኞችን ይጠብቃቸዋል።

ስለዚህም፣ ጌታ እግዚአብሔር ስለተናገረ፣ ድምጽህን ከፍ አድርገህ ከመናገር አትቆጠብ፣ ስለዚህ ትንቢትን ተናገር፣ እና ይህም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል አማካይነት ይሰጣል።

፲፩ እናም እምነት ካለህ፣ እነሆ፣ እስከምመጣ ድረስ እኔም ከአንተ ጋር ዘወትር እሆናለሁ—

፲፪ እናም እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ በቶሎም እመጣለሁ። እኔ ጌታህ እና ቤዛህ ነኝ። እንዲህም ይሁን። አሜን።