ክፍል ፶፬
በሰኔ ፲፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለኑወል ናይት የተሰጠ ራዕይ። በቶምሰን ኦሀዮ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የቤተክርስቲያኗ አባላት ስለ ንብረት መቀደስ ጉዳዮች አልተስማሙም ነበር። እራስን መውደድና ስግብግብነትም ይታዩ ነበር። ወደ ሼክርስ ሄዶበት ከነበረው ሚስዮን በኋላ (ክፍል ፵፱ መግቢያን ተመልከቱ)፣ ሊመን ኮፕሊም ትልቅ የእርሻ ስፍራውን ከኮልዝቪል ኒው ዮርክ ለሚመጡ ቅዱሳን በውርስ ለመባረክ የገባውን ቃል ሰብሮ ነበር። በዚህ ምክንያትም፣ (በቶምሰን ውስጥ የሚኖሩ አባላት መሪ) ኑወል ናይት እና ሌሎች ሽማግሌዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለመጠየቅ ነቢዩ ዘንድ መጥተው ነበር። ነቢዩም ጌታን ጠይቀ እናም በቶምሰን የሚኖሩትን አባላት ከሊመን ኮፕሊ እርሻ እንዲወጡ እና ወደ ምዙሪ እንዲጓዘ መመሪያ የሚሰጠውን ይህን ራዕይ ተቀበለ።
፩–፮፣ ምህረት ለማግኘት ቅዱሳን የወንጌሉን ቃል ኪዳን መጠበቅ አለባቸው፤ ፯–፲፣ በስቃይም ትዕግስተኛ መሆን አለባቸው።
፩ እነሆ፣ ጌታ፣ እንዲሁም ሀአልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው፣ እንዲሁም ለአለም ኃጢአት ለየተሰቀለው እንዲህ ይላል—
፪ እነሆ፣ በእውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ኑወል ናይት፣ በሾምኩህ ስልጣን ውስጥ ጸንተህ ቁም።
፫ እና ወንድሞችህ ጠላቶቻቸውን ለማምለጥ ፈቃድ ካላቸው፣ ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ንስሀ ይግቡ፣ እና በፊቴም በእውነት ሀትሁት እና የተዋረዱ ይሁኑ።
፬ እናም ለእኔ የገቡት ሀቃል ኪዳን ስለተሰበረ፣ ይህም ለከንቱ ሆኗል እናም ተሽሮአልም።
፭ እናም በእርሱ ጠንቅ ሀማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት፣ ወደ ጥልቅም ባሕር መሰጠም ይሻለው ነበርና።
፮ ቃል ኪዳንን የሚያከብሩት እና ትእዛዝን የሚከተሉት ግን የተባረኩ ናቸው፣ እነርሱም ሀምህረትን ያገኛሉና።
፯ ስለዚህ፣ ጠላቶቻችሁ እንዳይመጡባችሁ አሁን ሂዱ፣ ከአገሩም ሽሹ፤ እናም ተጓዙ፣ እና መሪያችሁ እና ገንዘቦችን እንዲከፍልላችሁ የምትሹትን ምረጡ።
፰ እንደዚሁም ወደ ምዕራብ ክፍለ ሀገሮች፣ ወደ ሀሚዙሪ ምድር፣ ወደ ላማናውያን ድንበርም ተጓዙ።
፱ ጉዟችሁን ከጨረሳችሁ በኋላም፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ስፍራን እስካዘጋጅላችሁ ድረስ፣ እንደ ሰዎች ሀየምትኖሩበትን ፈልጉ።
፲ እና ደግሞም፣ ሀእስክመጣ ድረስ በስቃይም ለትዕግስተኛ ሁኑ፤ እናም፣ እነሆ፣ በቶሎም እመጣለሁ፣ እና ደመወዜ ከእኔ ጋር ነው፣ እናም እኔን ተግተው ሐየሚሹኝም ለነፍሳቸው መእረፍትን ያገኛሉ። እንዲሁም ይሁን። አሜን።