ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸


ክፍል ፸

ህዳር ፲፪፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። የነቢዩ ታሪክ እንደሚገልጸው ከህዳር ፩ እስከ ፲፪ አራት ልዩ ጉባኤዎች ተካሂደዋል። በእነዚህም ስብሰባዎች ማብቂያ ላይ፣ በኋላም እንደ የ Book of Commandments (መፅሐፈ ትእዛዛት) እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የታተሙት ራዕዮች ታላቅ አስፈላጊነት ታሰበበት። ይህም ራዕይ የተሰጠው ጉባኤው እነዚህን ራዕዮች “ለቤተክርስቲያኗ ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ እንዳላቸው” በድምጽ ምርጫ ከተሰጠ በኋላ ነበር። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ስለዚህ ራዕይ “የአዳኛችን መንግስት ሚስጥር ቁልፎች ለሰው በአደራ እንደተሰጡ በማሳየት፣ በእነዚህ የመጨረሻዎቹ ቀናት የቤተክርስቲያኗ መሰረት፣ እና ለአለምም ጥቅም” የሚሆን ነው ብሎታል።

፩–፭፣ ራዕዮችን እንዲያትሙ መጋቢዎች ተመርጠዋል፤ ፮–፲፫፣ በመንፈሳዊ ነገሮች የሚያገለግሉ ደሞዛቸው ይገባቸዋል፤ ፲፬–፲፰፣ ቅዱሳን በስጋዊ ነገሮች እኩል መሆን አለባቸው።

እነሆ፣ እና አድምጡ፣ እናንት የፅዮን ኗሪዎች፣ እናም በሩቅ ያላችሁ የቤተክርስቲያኔ ህዝብ፣ እናም ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ ለአገልጋዬ ማርቲን ሀሪስ፣ እና ደግሞም ለአገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ደግሞም ለአገልጋዬ ጆን ዊትመር፣ ለአገልጋዬ ስድኒ ሪግደን፣ እና ደግሞም ለአገልጋዬ ውልያም ደብሊው ፌልፕስ በትእዛዝ መንገድ የምሰጣቸውን የጌታን ቃል ስሙ።

ትእዛዝ እሰጣቸዋለሁና፤ ስለዚህ፣ አድምጡ እናም ስሙ፣ ጌታ እንዲህ ይላቸዋልና—

እኔ ጌታ መርጫቸዋለሁ፣ እናም በሰጠኋቸው፣ እና ከዚህም በኋላ ለምሰጣቸው ራዕዮች እና ትእዛዛት መጋቢዎች እንዲሆኑ ሾሜአቸዋለሁ፤

እናም የዚህን የመጋቢነትን ዘገባ በፍርድ ቀን እፈልግባቸዋለሁ።

ስለዚህ፣ እኔም መርጫቸዋለሁ፣ እናም እነዚህን የሚመለከቱትን ጥቅሞቻቸውን፣ አዎን ቅሬታዎችን ማስተዳደር፣ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ ይህም ሀላፊነታቸው ነው።

ስለዚህ፣ እነዚህን ነገሮች ለቤተክርስቲያኗም ሆነ ለአለም እንዳይሰጡ ትእዛዝ እሰጣቸዋለሁ፤

ይሁን እንጂ፣ ከመሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው እና መሻታቸው በላይ እስከተቀበሉ ድረስ፣ ወደ ጎተራዬ ያግቡ፤

እናም፣ እንደ መንግስት ህግጋት ወራሾች እስከ ሆኑ ድረስ፣ ጥቅሙም ለፅዮን ኗሪዎች፣ እናም ለትውልዶቻቸው፣ የተቀደሰ ይሆናል።

እነሆ፣ ጌታ ከእያንዳንዱ ሰው፣ እንዲሁም እኔ ጌታ እንደመደብኩት ወይም ከዚህ በኋላ ለእያንዳንዱ ሰው እንደምመድበው፣ በመጋቢነቱ የምጠብቅበት ይህ ነው።

እናም እነሆ፣ በህያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል የሆነ ከእነዚህ የህግ ግዴታዎች ነጻ የሆነ ማንም የለም፤

፲፩ አዎን፣ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የጌታን ጎተራን የሚጠብቀው ወኪል፣ ወይም በስጋዊ ነገሮች ላይ መጋቢነት የተሰጠውም ቢሆን ከእነዚህ የህግ ግዴታዎች ነጻ አይደሉም።

፲፪ ለመንፈሳዊ ጉዳዮችንም ሊያስተዳድር የተመረጠውም፣ ለስጋዊ ጉዳዮች አስተዳደር መጋቢነት እንደተሰጣቸው ሁሉ፣ እርሱም ደሞዙ ይገባዋል፤

፲፫ አዎን፣ እንዲሁም በብዛትም፣ ይህ ብዛትም ለእነርሱ በመንፈስ መግለጥ በኩል ይጨመርላቸዋል።

፲፬ ይሁን እንጂ፣ በስጋዊ ነገሮች እኩል ሁኑ፣ እናም ይህንንም በመሰሰት አይደለም፣ አለበለዚያም፣ የመንፈስ መገለጥ ብዛቱ ይከለከላልና።

፲፭ በእዚህ እያሉ አገልጋዮቼ በረከቴ በላያቸው እንዲገለጥ እና በትጋታቸው ምላሽ እና ለደህንነታቸው እንዲሁም ለጥቅማቸው ይህን ትእዛዝም እሰጣቸዋለሁ፤

፲፮ ለምግብ እና ለልብስ፣ ለውርስ፣ ለቤቶች እና መሬትም እኔ ጌታ ባስቀመጥኳቸው ስፍራ ሁሉ እና በምልካቸው በማንኛቸውም ስፍራ ይሆኑ ዘንድ ይህን ትእዛዝም እሰጣቸዋለሁ።

፲፯ በብዙ ነገሮች ታማኝ ነበሩና፣ እናም ኃጢአትንም ባለመስራት ድረስ በጎን ነገር አድርገዋልና።

፲፰ እነሆ፣ እኔ ጌታ መሐሪ ነኝ እናም እባርካቸዋለሁ፣ እናም ወደ እነዚህ ነገሮች ደስታም ይገባሉ። እንዲህም ይሁን። አሜን።