ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳


ክፍል ፻፳

በሐምሌ ፰፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) በፋር ዌስት ሚዙሪ ከቀደመው ራዕይ፣ ክፍል ፻፲፱፣ የተጠቀሱት በአስራት የተሰጡትን ንብረቶችን ምን እንደሚደረግባቸው ለማሳወቅ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ።

በእውነት እንዲህ ይላል ጌታ፣ ለቤተክርስቲያኔ ቀዳሚ አመራር፣ እናለ ኤጲስ ቆጶስ እና ለሸንጎው፣ እና ለከፍተኛ ሸንጎዬ፣ እና በምሰጣቸውም በራሴ ድምጽ፣ ይህም በሸንጎው በጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ አሁን ነው፣ ይላል ጌታ። እንዲህም ይሁን። አሜን።

      • ይህም አስራት ማለት ነው።