ክፍል ፻፳፩
በመጋቢት ፳፣ ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) በልብረቲ ሚዙሪ በእስር ቤት ውስጥ እስረኛ ሆኖ እያለ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለቤተክርስቲያኗ በተሰጠ ደብዳቤ ውስጥ የተጻፉ ጸሎት እና ትንቢቶች። ነቢዩ እና አያሌ ባልንጀሮቹ በእስር ቤት ውስጥ ብዙ ወራትን አሳልፈው ነበር። ወደ ውሳኔ ሰጪ ዋና ሰዎችና ወደ ፍርድ ቤቶች የላኩት አቤቱታቸው እና ልመናቸው ምንም እርዳታ አላመጡላቸውም።
፩–፮፣ ነቢዩ ስለቅዱሳን ስቃይ ጌታን ለመነ፤ ፯–፲፣ ጌታም ለእርሱም ሰላምን ተናገረ፤ ፲፩–፲፯፣ በጌታ ህዝብ ላይ በሀሰት መተላለፍ ክስን የሚከሷቸው ሁሉ የተረገሙ ናቸው፤ ፲፰–፳፭፣ ለክህነት ስልጣን መብትም አይኖራቸውም እና ይኮነናሉ፤ ፳፮–፴፪፣ በብርታት ለሚጸኑትም የክብር ራዕዮች ቃል ተገብተውላቸዋል፤ ፴፫–፵፣ ለምን ብዙዎችም እንደተጠሩ እና ጥቂቶችም እንደተመረጡ፤ ፵፩–፵፮፣ ክህነትን በፅድቅ ብቻ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ።
፩ እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ? እና ሀየተሰወርክበትን ስፍራ የሚሸፍነው ድንኳን የት ነው?
፪ ሀእስከመቼ እጅህ፤ አይንህ አዎን ንጹህ አይኖችህ ከዘለአለማዊው ሰማይ በህዝብህ እና በአገልጋዮችህ ላይ የሚደረጉትን ክፋቶች እያዩ ለቅሶአቸውም ወደ ጆሮህ እያስተጋባ ትታገሳለህ?
፫ አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ ልብህ ለእነርሱ ከመለሳለሱ በፊት፣ እና ለእነርሱም አንጀትህ በርህራሄ እስከሚሞላ ድረስ ሀለስንት ጊዜ እነዚህን ክፋቶችን እና ህጋዊ ያልሆኑትን ጭቆናዎችን ይሰቃዩ።
፬ ሰማይን፣ እና ምድርን፣ እና ባህሮችን፣ እና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮችን ሁሉ ፈጣሪው፣ እና ዲያብሎስን እና ጥቁር እና ያጨለመውን የሲኦል ግዛት የምትቆጣጠር እና በቁጥጥር ስር የምታደርግ ሀሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ—እጅህን ዘርጋ፤ አይንህም በትኩረት ይመልከት፤ ድንኳንህም ይነቀል፤ ለየተሰወርክበትም ስፍራ አይሸፈን፤ ጆሮህም ያዘንብል፤ ልብህም ይለሳለስ፣ እና አንጀትህም በርህራሄ ወደ እኛ ይሞላ።
፭ ቁጣህም በጠላቶቻችን ላይ ይቀጣጠል፤ እና በልብህ ቁጣ፣ በጎራዴህ ክፉት ስለተደረጉብን ሀተበቀልልን።
፮ አምላካችን ሆይ፣ የሚሰቃዩትን ቅዱሳንህን አስታውስ እና አገልጋዮችህም በስምህ ለዘለአለም ይደሰታሉ።
፯ ልጄ፣ ለነፍስህ ሰላም ይኑርህ፤ ሀጭንቀትህ እና ስቃይህ ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው፤
፰ ከዚያም፣ በመልካም ይህን ሀብትጸና፣ እግዚአብሔርም ወደ ላይ ዘለአለማዊ ክብር ይሰጥሀል፤ ጠላቶችህንም በሙሉ ታሸንፋቸዋለህ።
፱ ሀባልንጀሮችህ በአጠገብህ ቆመዋል፣ እና በሞቀ ልብ እና በጓደኝነት እጆች እንደገናም ሰላምታ ይሰጡሀል።
፲ እንደ ሀኢያብም ገና አይደለህም፤ ባልንጀሮችህ በኢያብ እንዳደረጉትም በአንተም ላይ በተቃራኒነት አይጣሉህም፣ ወይም በመተላለፍ አይከሱህም።
፲፩ እና በመተላለፍ የሚከሱህም፣ ተስፋቸው ይከስማል፣ እና በምትወጣው ጸሀይ በሚያነድ ጨረር እንደሚቀልጥ ሀበረዶም፣ ተስፋ ያደረጉበትም ነገር ይጠፋል፤
፲፪ ደግሞም እግዚአብሔር እጁም ተገልጧል እና ድንቅ ስራዎቹ እንዳይገቧቸው ዘንድ ሀጊዜያትን እና ዘመናትን ለመቀየርና አዕምሮዎቻቸውን ያጨልም ዘንድ፤ ደግሞም እንዲያረጋግጥላቸውም እና በአታላይነታቸው ይይዛቸው ዘንድ አትሟል፤
፲፫ ደግሞም ልቦቻቸው የረከሱ ስለሆኑ፣ እና በሌሎች ላይ ክፉ ነገሮች እንዲወድቅባቸው ፈቃደኛ ስለሆኑ፣ እና ሌሎች እንዲሰቃዩ ለማድረግ ስለሚወዱ፣ ይህም ሀበእነርሱ ላይ በሚበልጥ መጠን ይመጣባቸዋል፤
፲፬ ተስፋ ያጡ ዘንድ፣ እና ተስፋቸውም እንዲቆረጥ፤
፲፭ እና ከዚህ ጊዜ አያሌ አመታት ሳያልፉም፣ እነርሱ እና መጪዎቹ ትውልዶቻቸው ከሰማይ በታች ይጠረጋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ማናቸውም በግድግዳው ቆመው አይቀሩም።
፲፮ በእኔ ሀበተቀቡት ላይ ተረከዛቸውን የሚያነሱት፣ ይላል ጌታ፣ እና ምንም እንኳን በአይኖቼ ብቁ የሆኑትን እና ያዘዝኳቸውን የሚያደርጉትን፣ በፊቴ ኃጢአትን ያልሰሩት ለኃጢአት ሰርተዋል በማለት የሚጮሁት ሁሉ የተረገሙ ናቸው፣ ይላል ጌታ።
፲፯ ነገር ግን ስለመተላለፍ የሚጮሁት ይህን የሚያደርጉት የኃጢአት አገልጋዮች እና ራሳቸውም የአመጸኞች ሀልጆች ስለሆኑ ነው።
፲፰ እና ወደባርነት እና ወደ ሞት ያመጧቸው ዘንድ በአገልጋዮቼ ላይ በሀሰት የሚመሰክሩትም—
፲፱ ወዮላቸው፤ ታናናሾቼን ሀስለሚያሰናክሉ ከቤቴ ለስርዓቶች ይቆረጣሉ።
፳ ሀቅርጫታቸውም አይሞላም፣ ቤታቸውና ጎተራዎቻቸውም ይጠፋሉ፣ እና እራሳቸውም በሚያባብሏቸው ይጠላሉ።
፳፩ እነርሱ ወይም መጪዎቹ ትውልዶቻቸውም ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ሀለክህነት ስልጣንም መብት አይኖራቸውም
፳፪ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቶቻቸው ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስመጥ ሀበተሻላቸው ነበር።
፳፫ ህዝቤን እንዳይመቻቸው ለሚያደርጉም፣ እና ለሚያሳድዷቸው፣ እና ለሚገድሏቸው፣ እና በእነርሱም ላይ ለሚመሰክሩባቸው ሁሉ ወዮላቸው ይላል የሰራዊት ጌታ፤ ሀየእፉኝት ልጆች ከገሀነም ፍርድ አያመልጡም።
፳፬ እነሆ፣ አይኖቼ ሀያያሉ እና ስራቸውን ሁሉ አውቃለሁ፣ እና ለሁሉም በጊዜውም ፈጣን ለፍርድም አኑሬላቸዋለሁ፤
፳፭ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሀስራው የተመደበለት ለጊዜ አለውና።
፳፮ እግዚአብሔር ሀእውቀቱን ለበቅዱስ መንፈሱ፣ አዎን አለም ከነበረበት እስከ አሁንም ድረስ ባልተገለጠውን፣ ለመናገርም የማይቻለውን የመንፈስ ቅዱስ ሐስጦታውን ይሰጣችኋል፤
፳፯ በመጨረሻዎቹ ዘመናት እንዲገለጡ የቀደሙት አባቶቻችን በጉጉት የጠበቋቸውን፣ ለክብራቸው ሙላት በኋላም የተጠበቁትን በመላዕክት ሀሳብ የተመሩበትን እውቀት ይሰጣችኋል፤
፳፰ እነርሱ ስለሚገለጡ፣ አንድ አምላክም ይኑር ብዙ ሀአማልክት፣ ይህም ለማንኛውም ነገር የማይሰወርበት ጊዜ ነው።
፳፱ ዙፋናት ቢሆኑ እና ጌትነት እና አለቅነት እና ሥልጣናት ሁሉ ሀይገለጣሉ እና ለኢየሱስ ክርስቶስም ወንጌል በብርታት ለጸኑት ሁሉ ይሰጧቸዋል።
፴ ደግሞም፣ ለሰማያት ወይም ለባህሮች፣ ወይም ለደረቅ መሬት፣ ወይም ለጸሀይ፣ ጨረቃ፣ ወይም ለከዋክብት ሀገደብ ቢሆን—
፴፩ የሚዞሩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በተመደቡላቸው ቀናት፣ ወራት፣ እና አመታት ሁሉ፣ እና በየቀናቶቻቸው ቀናት፣ ወራት፣ እና አመታት ሁሉ፣ እና በክብሮቻቸው፣ በህግጋታቸው፣ እና በተወሰኑት ጊዜያቶቻቸው ሁሉ፣ ሀበዘመን ፍጻሜ ቀናት ሁሉ ይገለጣሉ—
፴፪ ሁሉም ሰው ወደ ሀዘለአለማዊነቱ እና ወደ ህያው ለእረፍቱ ሲገቡ፣ እስከመጨረሻው እና ለዚህ መጨረሻም ይጠበቅ ዘንድ፣ ከዚህ አለም በፊት በሌሎች አማልክት ዘለአለማዊ ሐአምላክ መሸንጎ መካከል በተመደበው መሰረት ያም ሊሆን ይገባዋል።
፴፫ እስከመቼ ጊዜ የሚደበላለቀው ውሀ ንጹህ ሆኖ ሊቆይ ይቻለዋል? የትኛውስ ሀይል ሰማያትን ሊያቆም ይችላል? በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ራሶች ላይ ሁሉን የሚገዛው ከሰማይ ሀእውቀቶችን ማፍሰሱን ከሚያቆም፣ ሰው ደካማ ክንዶቹን ዘርግቶ የሚዙሪን ወንዝ ከተወሰነለት መንገዱ ያቆም ዘንድ ወይም ተቃራኒው እንዲዞር ለማድረግ ቢሞክር ይቀለዋል።
፴፬ እነሆ፣ ብዙዎች ሀተጠርተዋል፣ ነገር ግን ለየተመረጡት ጥቂቶች ናቸው። እና ያልተመረጡትስ ለምንድን ነው?
፴፭ ምክንያቱም ልባቸውን ሀበአለም ነገሮች ላይ ስለሚያደርጉ እና በሰዎች ለይሞገሱ ዘንድ ስለሚነሳሱ፣ ይህን አንድ ትምህርት አይማሩም—
፴፮ የክህነት ሀመብቶች እና የሰማይ ሀይላት የማይነጣጠሉ ናቸው፣ እና የሰማይ ለሀይላት ሐበፅድቅ መሰረታዊ መርሆች የሚካሄድ ካልሆነ በስተቀር ሊቆጣጠሯቸው እና ሊጠቀሙባቸውም ዘንድ አይቻልም።
፴፯ ለእኛ ሊሰጡን መቻሉ እውነት ነው፤ ነገር ግን ሀኃጢአታችንን ለለመሸፈን፣ ወይም ሐኩራታችንን እንዲሁም ከንቱ ፍላጎታችንን ለማርካት፣ ወይም በማንኛውም የፅድቅ ባልሆነ መንገድ በሰዎች ልጆች ነፍሳት ላይ ቁጥጥር ወይም የበላይነትን ወይም ግዴታን ለማድረግ ብንሞክር፣ እነሆ፣ ሰማያት ራሳቸውን መያገልላሉ፤ የጌታም መንፈስም ያዝናል፤ እና ይህ ሲወሰድም፣ የሰው ክህነት ወይም ስልጣን ፍጻሜ ይሆናል።
፴፰ እነሆ፣ ይህን ከማወቁም በፊት፣ የመውጊያውን ብረት ሀይቃወም ዘንድ፣ ቅዱሳንን ለያሳድድ፣ እና ከእግዚአብሔርም ጋር ይዋጋ ዘንድ ብቻውን ይተዋል።
፴፱ ወዲያውኑም ትንሽ ስልጣን ያገኙ ሲመስላቸው፣ ፈጥነው ጻድቅ ባልሆነ ሁኔታ በበላይነት ስልጣናቸውን ሲጠቀሙበት፣ ይህም የሰው ሁሉ ሀተፈጥሮ እና ባህርይ መሆኑንም ከአሳዛኝ አጋጣሚዎች ተምረናል።
፵ ስለዚህ፣ ብዙዎች ተጠርተዋል፣ ግን የተመረጡት ጥቂቶች ናቸው።
፵፩ ሀበማሳመን፣ ለበትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሀይል ወይም ተጽዕኖ በክህነት ስልጣን ዘዴ ሊደገፍ አይቻልም ወይም አይገባውም፤
፵፪ ይህም በርህራሄ፣ እና ሀያለግብዝነትና ለያለተንኮል መንፈስን በታላቅ በሚያሳድግ ንጹህ እውቀት ብቻ ነው ሊደገፍ የሚችለው፤
፵፫ መንፈስ ቅዱስ በሚነሳሳበት በትክክለኛው ጊዜ በሀያልነት ሀበመቆጣት፤ ከዚያም በኋላ እንደጠላት እንዳያይህ፣ ለተቆጣኸውም ተጨማሪ ለፍቅር አሳይ፤
፵፬ በእዚህም እምነትህ ከሞት ሀይል በላይ እንደሆነ ይወቅ።
፵፭ አንጀትህም ለሁሉም ሰው እና ለእምነት ቤተ ሰዎች በልግስና ይሞላ፣ እና ሀምግባረ በጎነትም ሳያቋርጥ ለአስተሳሰብህን ያሳምር፤ ከዚያም ልበ ሙሉነትህ በእግዚአብሔር ፊት እየጠነከረ ይሄዳል፤ እና የክህነት ትምህርትም በነፍስህ ላይ እንደ ሰማይ ሐጠል ትንጠባጠብልሀለች።
፵፮ ሀመንፈስ ቅዱስም የዘወትር ባልንጀራህ ይሆናል፣ እና በትርህም የማይቀየር የፅድቅ እና የእውነት በትር ይሆናል፤ እና ለስልጣንህም ዘለአለማዊ ስልጣን ይሆናል፣ እና በማያስገድድ ዘዴም ይህም ወደ አንተ ለዘለአለም ይፈሳል።