ክፍል ፴፱
ጥር ፭፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በፈየት ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለጄምስ ኮቪል የተሰጠ ራዕይ። ለአርባ አመታት የሜተዲስት ቄስ የነበረው ጄምስ ኮቪል ጌታ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የሚሰጠውን ማንኛውንም ትእዛዝ ለማክበር ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።
፩–፬፣ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ኃይል አላቸው፤ ፭–፮፣ ወንጌልን መቀበል ክርስቶስን መቀበል ነው፤ ፯–፲፬፣ ጄምስ ኮቪል እንዲጠመቅ እና በጌታ የወይን ስፍራ እንዲሰራ ታዘዘ፤ ፲፭–፳፩፣ የጌታ አገልጋዮች ከዳግም ምጽአት በፊት ወንጌልን ይስበኩ ፳፪–፳፬፣ ወንጌልን የሚቀበሉ ለጊዜአዊ እና ለዘለአለም ይሰባሰባሉ።
፩ ሀከዘለአለም እስከዘለአለም ህያው የሆንኩትን ታላቁ ለእኔ ነኝን፣ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን ድምፅ አድምጥ እናም ስማ—
፪ በጨለማ የሚያበራውን እና በጨለማም ያሉት የማይረዱበት፣ የአለም ሀብርሀን እና ህይወት የሆነውን፤
፫ ሀበመካከለኛው ዘመን የእኔ ወደሆኑት መጣሁ እና የእኔም የሆኑትም አልተቀበሉኝም፤
፬ ነገር ግን ለተቀበሉኝ ሁሉ ሀልጆቼ ይሆኑ ዘንድ ኃይልን ሰጠኋቸው፤ እናም ለሚቀበሉኝም እንዲሁ፣ ልጆቼ እንዲሆኑ ኃይልን እሰጣቸዋለሁ።
፭ እናም እውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ ወንጌሌን ሀየሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እናም ወንጌሌን የማይቀበል እኔን አይቀበልም።
፮ እናም ይህ የእኔ ሀወንጌል ነው—የንሰሀና የውሀ ጥምቀት፣ እናም በመቀጠል ሁሉን ነገሮችን የሚያሳየውንና የመንግስተ ስማይን ስላማዊ ነገሮችን ለየሚያስተምረውና አጽናኝ የሆነው፣ ሐየእሳት እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይከተላል።
፯ እናም አሁን፣ እነሆ፣ አገልጋዬ ሀጄምስ እልሀለሁ፣ ስራዎችህን ተመልክቻለሁ እናም አውቅሀለሁ።
፰ እናም እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ ወቅት ልብህ በፊቴ የቀና ነው፤ እናም፣ እነሆ፣ በራስህም ላይ ታላቅ በረከቶችን አድርጌአለሁ፤
፱ ሆኖም፣ በመታበይ እና ሀበአለም ነገሮች ምክንያት ብዙ ጊዜ ስላልተቀበልከኝ፣ ታላቅ መከራን አይተሀል።
፲ ነገር ግን፣ እነሆ፣ ተነሳና ሀተጠመቅ፣ እናም ስሜንም እየጠራህ ኃጢአቶችህን እጠብ፣ መንፈሴንና የማታውቀውን ታላቅ በረከትን ትቀበላለህ የሚለውን ድምጼንም የምታደምጥ ከሆነ የመዳንህ ቀናት መጥተዋል።
፲፩ እናም ይህን የምታደርግ ከሆነ፣ ለታላቅ ስራ አዘጋጅቼሀለሁ። በዚህ የመጨረሻው ቀናት የላክሁትን የወንጌሌን ሙላት፣ እንዲሁም የእስራኤል ቤት የሆኑትን ህዝቤን ሀእንዲመለሱ ለማድረግ የላክሁትን ቃል ኪዳን ትሰብካለህ።
፲፪ እናም እንዲህም ይሆናል ኃይልም በአንተ ላይ ሀይሆናል፤ ታላቅ እምነትም ይኖርሀል፣ እናም ከአንተም ጋር እሆናለሁ፣ ከፊትህም እሄዳለሁ።
፲፫ በወይን ስፍራዬም ሀእንድትሰራ፣ እናም ቤተክርስቲያኔን ትገነባ፣ እና በከፍታዎችም ላይ እንድታብብና ሀሴትንም ለታደርግ ዘንድ ፅዮንን ሐለማምጣት ተጠርተሀል።
፲፬ እነሆ፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ወደ ኦሀዮ እንድትሄድ እንጂ፣ ወደ ምስራቅ ሀገሮች እንድትሄድ አልተጠራህም።
፲፭ እናም በኦሀዮ ህዝቤ ራሳቸውን እስካሰባሰቡ ድረስ፣ በሰዎች ልጆች መካከል የማይታወቅን ሀበረከትን አስቀምጫለሁ፣ እናም በራሶቻቸውም ላይ ይፈሳል። ከዚያም ወንዶቹ ለበህዝብ ሐሁሉ መካከል ይሄዳሉ።
፲፮ እነሆ፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ እጄን በፍርድ በህዝብ ላይ ከማድረግ እንደምቆጠብ በማሰብ፣ በኦሀዮ የሚገኙ ህዝብ በታላቅ እምነት ወደ እኔ ይጣራሉ፣ ነገር ግን ቃሌን አልክድም።
፲፯ ስለዚህ፣ ለመጨረሻም ጊዜ ሀይገረዝ ዘንድ፣ በታላቅ ኃይልህ ስራህን ጀምር እናም ታማኝ ሰራተኞችን ወደ ወይን ስፍራዬ ጥራ።
፲፰ እናም ንሰሀ እስከገቡና የወንጌሌን ሙላት እስከተቀበሉ እንዲሁም እስከተቀደሱ ድረስ፣ እጄን ሀበፍርድ ከማድረግ እቆጠባለሁ።
፲፱ ስለዚህም፣ ከፍ ባለ ድምጽም፣ መንግስተ ሰማይ ቀርባለች በማለት፥ ሆሳዕና! የልዑል እግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ብለህ በመጮህ ወደፊት ሂድ።
፳ ሀለምፅዓቴም ቀን ከፊት ለፊቴ መንገድን በማዘጋጀት፣ በውሀ በማጥመቅ ወደፊት ሂድ፤
፳፩ ጊዜው ተቃርቧልና፤ ሀቀኑን እና ሰአቱን ማንም ሰው ለአያውቅም፤ ነገር ግን በእርግጥም ይመጣል።
፳፪ እና እነዚህንም ነገሮች የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እናም ለጊዜውና ለዘለአለም ወደ እኔ ይሰበሰባሉ።
፳፫ እናም ዳግም፣ እንዲህም ይሆናል በውሀ ባጠመቅሀቸው ሁሉ ላይ፣ ሀእጆችህን ትጭናለህ፣ እናም የመንፈስ ቅዱስን ለስጦታ ይቀበላሉ፣ እንዲሁም ሐየምጽአቴን ቀን ምልክቶች መይጠባበቃሉ እናም እኔንም ያውቃሉ።
፳፬ እነሆ፣ በቶሎም እመጣለሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።