ክፍል ፺፯
በነሀሴ ፪፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዩ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ፣ ነቢዩ ጌታን ለመረጃ በጠየቀበት መልስ፣ የፅዮን፣ የጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ ቅዱሳን ጉዳዮችን የሚያመራምር ነበር። በዚህ ጊዜ በሚዙሪ የነበሩት የቤተክርስቲያኗ አባላት በጥልቅ እየተሰቃዩ ነበር እና በሐምሌ ፳፫፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ከጃክሰን የግዛት ክፍል ወጥተው እንዲሄዱ ስምምነትን እንዲፈርሙ ተገድደው ነበር።
፩–፪፣ ብዙዎቹ የፅዮን (ጃክሰን የግዛት ክፍል፣ ሚዙሪ) ቅዱሳን በእምነታቸው ተባርከዋል፤ ፫–፭፣ ፓርሊ ፒ ፕራት በፅዮን ትምህርት ቤት እንዲያገለግል ታዝዟል፤ ፮–፱፣ ቃል ኪዳናቸውን የሚያከብሩትን ጌታ ይቀበላቸዋል፤ ፲–፲፯፣ ልበ ንጹ የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያዩበት ቤት በፅዮን ይሰራ፤ ፲፰–፳፩፣ ፅዮን ልበ ንጹህ ነች፤ ፳፪–፳፰፣ ታማኝ ከሆነች ፅዮን የጌታን ቅጣት ታመልጣለች።
፩ ባልንጀሮቼ እውነት እላችኋለሁ፣ በእውነት ትሁት ሆነው እና በቅንነት ጥበብን ለመማርና እውነትን ለማግኘት ስለሚጥሩት ብዙዎች፣ ሀበፅዮን ምድር ስላሉት ወንድሞቻችሁ ያለኝን ፈቃድ አሳያችሁ ዘንድ በድምጼ፣ እንዲሁም በመንፈሴ ድምፅ እናገራችኋለሁ።
፪ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እንደነዚህ አይነቶች የተባረኩ ናቸው፣ ያገኙታልና፤ ፍርድንም ሳመጣባቸው ፅድቅ አደርግ ዘንድ፣ እኔ ጌታ ሀለቅን እና ለምፈልገው ሁሉ ምህረትን አሳያለሁና።
፫ እነሆ፣ በፅዮን ስላለው ሀትምህርት ቤት እላችኋለሁ፣ እኔ ጌታ በፅዮን ትምህርት ቤት በመኖሩ፣ ደግሞም በአገልጋዬ ለፓርሊ ፒ ፕራትም ተደስቻለሁ፣ እርሱም በእኔ ይኖራልና።
፬ በእኔ በመኖር የሚቀጥል ቢሆን ሌላ ትእዛዛትን እስከምሰጠው ድረስ በፅዮን ምድር ትምህርት ቤት ውስጥ በመሪነት ይቀጥላል።
፭ እናም ለትምህርት ቤቱ፣ እና ለፅዮን ውስጥ ቤተክርስቲያን መታነጽ ቅዱሳን መጻህፍትን ሁሉ እና ሚስጥራትን ለማብራራት በሚበዙ በረከቶች እባርከዋለሁ።
፮ እና ለሚቀሩት ትምህርት ቤትም፣ እኔ ጌታ፣ ምህረትን ለማሳየት ፈቃደኛ ነኝ፤ ይህም ቢሆን፣ ሀመገሰፅ የሚያስፈልጋቸው ሌሎችም አሉ፣ እና ስራዎቻቸውም እንዲታወቁ ይደረጋል።
፯ ሀምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እና መልካም ለፍሬ የማይሰጥ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል እና ወደ እሳትም ይጣላል። እኔ ጌታ ተናግሬዋለሁ።
፰ እውነት እላችኋለሁ፣ በመካከላቸው ሀልቦቻቸው ለታማኝ እንደሆኑ፣ እና እንደተሰበሩ፣ እና መንፈሶቻቸው እንደተዋረዱ የሚያውቁ፣ እና ቃል ኪዳኖቻቸውን ሐበመስዋዕት—አዎን፣ እኔ ጌታ በማዝዘው እያንዳንዱ መስዋእት—ለመከተል መፈቃደኛ የሆኑት ሁሉ፣ እኔ ሠእቀበላቸዋለሁ።
፱ እኔ ጌታ በመልካም ምድር ውስጥ፣ በንጹህ ወንዝ አጠገብ እንደተተከለ፣ ውድ ፍሬዎች እንደሚሰጥ፣ በጣም ፍሬአማ እንደሆነ ዛፍ እንዲፈሩ አደርጋለሁ።
፲ እውነት እላችኋለሁ፣ በፅዮን ምድር ውስጥ በሰጠኋችሁ ሀንድፍ መሰረት ለቤት ይሰራልኝ ዘንድ ፍቃዴ ነው።
፲፩ አዎን፣ በቶሎም በህዝቤ አስራት ይሰራ።
፲፪ እነሆ፣ ለፅዮን ደህንነት ሀቤት ለእኔ ይሰራ ዘንድ፣ ከእጆቻቸው እኔ ጌታ የምጠብቅባቸው ለአስራትና መስዋዕት ይህ ነው—
፲፫ ለቅዱሳን ሁሉ ሀምስጋናን የማቅረቢያ ቦታ፣ እና በአገልግሎቱ ስራ በተለያዩት ጥሪአቸው እና ሀላፊነታቸው የተጠሩት ሁሉ የሚማሩበት ቦታ፤
፲፬ በአገልግሎታቸው፣ በአስተያየታቸው፣ በመሰረታዊ መርህ፣ እና በትምህርታቸው፣ እና በላያችሁ የተሰጣችሁ የመንግስቱ ሀቁልፍ፣ በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር ለመንግስትን በሚመለከት ሁሉ፣ በዚህ ሁሉ ፍጹም ሐመረዳት ይኖራቸው ዘንድ ነው።
፲፭ እና በጌታ ስም ቤትን ለእኔ እስከሰሩልኝ ድረስ፣ እና እንዳይረከስ፣ ማንኛውንም ሀእርኩስ ነገር እንዲገባበት እስካልፈቀዱ ድረስ፣ ለክብሬ ያርፍበታል፤
፲፮ አዎን፣ እና በዚያም ሀእገኛልሁ፣ እመጣበታለሁና፣ እና የሚገባበት ለንጹህ ልብ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያያል።
፲፯ ነገር ግን የረከሰ ቢሆን አልመጣበትም፣ እና ክብሬም አይገኝበትም፤ ቅዱስ ወዳልሆነ ቤተመቅደስ አልመጣምና።
፲፰ እሁንም እነሆ፣ ፅዮን እነዚህን ነገሮች ካደረገች ሀትበለፅጋለች፣ እና ታድጋለችም እናም በጣም የከበረች፣ በጣም ታላቅ፣ እና በጣም አስፈሪም ትሆናለች።
፲፱ እና የምድር ሀህዝብም ያከብሯታል፣ እና እንዲህም ይላሉ፥ በእርግጥም ለፅዮን የእግዚአብሔር ከተማ ነች፣ እና በእርግጥም ፅዮን ልትወድቅ አትችልም፣ ወይም ከስፍራዋ አትወጣም፣ እግዚአብሔር በዚያ ነውና፣ እና የጌታም እጅ በዚያ ነው፤
፳ እና በጉልበቱ ሀይል መድሀኒቷና ታላቅ ሀማማዋ እንደሚሆን መሀላ ገብቷል።
፳፩ ስለዚህ፣ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፣ ሀፅዮን ትደሰት፣ ይህች ፅዮን ነውና—ልበ ንጹህ፤ ስለዚህ፣ ኃጥአን ሁሉ ሲያዝኑ ፅዮን ትደሰት።
፳፪ እነሆም፣ እና አስተውሉ፣ በኃጢአተኞቹ ላይ ሀበቀል እንደ አውሎ ንፋስ ፈጥኖ መጥቷል፤ እና ማንስ ያመልጠዋል?
፳፫ የጌታ ሀመከራም ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ ወሬውንም መላውን ህዝብ ያስደነግጣል፤ አዎን፣ ጌታ እስከሚመጣም አይቆምም፤
፳፬ የጌታ ቁጣ በርኩሰታቸውና በክፉ ስራዎቻቸው ሁሉ ላይ ተቀጣጥሏልና።
፳፭ ይህም ቢሆን፣ ፅዮን ያዘዝኳትን ማንኛውም ነገሮች ሁሉ የምትከተል ከሆነችም ሀታመልጣለች።
፳፮ ነገር ግን፣ ያዘዝኳትን ማንኛውም ነገሮች ሁሉ ባትከተል ግን፣ በሁሉም ስራዎቿ መሰረት በታላቅ ስቃይ፣ ሀቸነፈር፣ መቅሰፍት፣ በጎራዴ፣ ለበበቀል፣ ሐበምትበላም እሳት መእጎበኛታለሁ።
፳፯ ይህም ቢሆን፣ እኔ ጌታ መስዋዕቴን እንደተቀበልኩ በጆሮዋ ይህ አንድ ጊዜ ይነበብላት፤ እና ኃጢአት ከዚህ በኋላ የማትሰራ ቢሆን ከእነዚህ ነገሮች ሀማንኛቸውም አይደርሱባትም።
፳፰ እና በበረከቶች ሀእባርካታለሁ፣ እና በእርሷና በትውልዶቿ ላይ ለዘለአለም የሚሆኑ በረከቶች አበዛላታለሁ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ። አሜን።