ክፍል ፻፴፯
በጥር ፳፩፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ በቤተመቅደስ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ጊዜውም በዚያ ጊዜ ቤተመቅደስን ለመምረቅ በመዘጋጀት ስርዓቶችን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ነበር።
፩–፮፣ ነቢዩ ወንድሙን አልቭንን በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ አየ፤ ፯–፱፣ የሙታን ደህንነት ትምህርት ተገለጠ፤ ፲፣ ሁሉም ልጆች በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ይድናሉ።
፩ ሀሰማያት ተከፈቱልን፣ እና የእግዚአብሔርን ለሰለስቲያል መንግስትን እና የእዚያን ክብር አየሁ፣ ሐበሰውነት ይሁን ከዚያ ውጪ አላወቅሁም።
፪ በእሳት ሀነበልባል የተከበበው፣ የዚያ መንግስት ወራሾች የሚገቡበት ለበር በጣም ታላቅ ውበት እንዳለውም አየሁ።
፫ ደግሞም ሀአብና ለወልድ የሚቀመጡበትን በጣም ብሩህ የሆነውን የእግዚአብሔር ሐየክብር ዙፋንንም ተመለከትኩ።
፬ ሀበወርቅ ምንጣፍ አምሳል የሆኑትን የመንግስቱን ውብ መንገዶችንም አየሁ።
፭ አባት ሀአዳምን እና ለአብርሐምንም፤ እና ሐአባቴና መእናቴንም፤ ለብዙ ጊዜ ሞቶ የነበረው ወንድሜ ሠአልቭንንም አየሁ።
፮ እና ጌታ እስራኤልን ሀዳግም ለመሰብሰብ እጁን ከመዘርጋቱ በፊት ከዚህ ህይወት ሄዶ ስለነበረ፣ እና ለኃጢአት ስርየት ለስላልተጠመቀ፣ በዚያ መንግስት ውስጥ እንዴት ሐውርስ እንዳገኘም ተደነቅሁኝ።
፯ እንዲህም ሲል የጌታ ሀድምፅ ወደ እኔ መጣ፥ ለመቆየት ቢፈቀድላቸው ይቀበሉት የነበሩት፣ ይህን ወንጌል ለባለማወቅ የሞቱት ሁሉ የእግዚአብሔር ሐሰለስቲያል መንግስት መወራሾች ይሆናሉ።
፰ ደግሞም በሙሉ ልባቸው ይህን ሀይቀበሉ የነበሩ፣ ካለዚህ እውቀት ከዚህ በኋላ የሞቱት ሁሉ የዚያ መንግስቱ ወራሾች ይሆናሉ፤
፱ እኔ ጌታ ሁሉንም ሰዎች ሀበስራዎቻቸው መሰረት፣ እንደልባቸውም ለምኞት ሐእፈርድባቸዋለሁና።
፲ እና በተጠያቂነት ሀእድሜም ከመድረሳቸው በፊት የሞቱትን ልጆች ሁሉ በሰማይ ሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ለእንደዳኑም ተመለከትኩኝ።