ክፍል ፳፮
በሐምሌ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒያ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ለኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ለጆን ዊትመር የተሰጠ ራዕይ። (የክፍል ፳፬ ርዕስን ተመልከቱ)።
፩ ቅዱሳን መጻህፍትን እንዲያጠኑ እና እንዲሰብኩ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ ፪፣ የጋራ ስምምነት ህግ ጸደቀ።
፩ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ ወደ ምዕራብ የሚቀጥለውን ጉባዔ ለማድረግ እስክትሄዱ ድረስ ጊዜአችሁን በቅዱሳን መጻህፍት ሀጥናት፣ ስብከት፣ ለበኮለስቪል ያለውን ቤተክርስቲያን በማጠንከር፣ በምድሩ ላይ ስራችሁን እንድታከናውኑ ይጠበቅባችኋል፣ እናም በመቀጠልም ምን እንደምታከናውኑ ይነገራችኋል።
፪ እናም ሁሉም ነገሮች በቤተክርስቲያን ሀበጋራ ስምምነት፣ በብዙ ጸሎት እና እምነት ይከናወናሉ፣ ሁሉንም ነገሮች በእምነት ትቀበላላችሁ። አሜን።