ክፍል ፵፱
በግንቦት ፯፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ ለስድኒ ሪግደን፣ ለፓርሊ ፒ ፕራት፣ እና ለሊመን ኮፕሊ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ሊመን ኮፕሊ ወንጌልን ተቀብሎ ነበር፣ ነገር ግን ቀደም ሲል አባል የነበረበትን የሼከሮቹን [የተወዛዋዦቹ] (ዩናይትድ ሶሳይቲ ኦፍ ብሊቨርስ እን ክራይስትስ ሰክንድ አፒሪንግ [በክርስቶስ ዳግም ምፅዓት የሚያምኑ የአንድነት ህብረተሰብ]) አንዳንድ ትምህርቶችን ይዞ ነበር። አንዳንዶቹ የሼከሮቹ እምነቶች የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ሲል እንደተከሰተ፣ እና አን ሊ በምትባል ሴት አምሳል እንደተገለጠ ነበር። የውሀ ጥምቀት እንደ አስፈላጊ ድርገት አይመለከቱትም ነበር። ጋብቻን አስወግደው፣ ግብረ ስጋ በማይፈጸምበት ኑሮ ያምኑ ነበር። አንዳንድ ሼከሮችም ስጋ መብላትን ይከለክሉ ነበር። ለዚህ ራዕይ መቅድምም፣ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንዲህ ይገልጻል፣ “ስለ ርዕሱ ፍጹም እውቀት ለማግኘት፣ ጌታን ጠየቅሁ፣ እናም የሚከተለውን ተቀበልሁ።” ራዕዩም የሼከሮቹ ቡድን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦችን ያፈርሳል። ከዚህ በፊት የተጠቀሱት ወንድሞችም ይህን ራዕይ (ክሊቭላንድ ኦሀዮ አካባቢ ላለው) ወደ ሼከሮቹ ማህብረሰብ ወስዱት፣ እና ለእነርሱም ሁሉንም አነበቡላቸው፣ ነገር ግን አልተቀበሉትም ነበር።
፩–፯፣ የክርስቶስ ምጽአት ቀንና ሰአት እርሱ እስከሚመጣ ድረስ አይታወቅም፤ ፰–፲፬፣ ደህንነትን ለማግኘት፣ ስዎች ንስሀ መግባት፣ በወንጌሉ ማመን፣ እና ስርዓቶችን ማክበር አለባቸው፤ ፲፭–፲፮፣ ጋብቻ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው፤ ፲፯–፳፩፣ ስጋን መመገብ የተፈቀደ ነው፤ ፳፪–፳፰፣ ከክርስቶስ የዳግም ምፅአት በፊት፣ ፅዮን ትበለፅጋለች እና ላማናውያንም እንደ ፅጌረዳ ያብባሉ።
፩ አገልጋዮቼ ስድኒ፣ ፓርሊ፣ እና ሊመን ቃሌን አድምጡ፤ እነሆም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የተቀበላችሁትን ወንጌሌን፣ እንደተቀበላችሁ እንዲሁ፣ ወደ ሼከሮቹ ሄዳችሁ ሀእንድትሰብኩላቸው ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ።
፪ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ሙሉ እውነትን ሳይሆን ከፈሉን ብቻ ለማወቅ ይሻሉ፣ ንስሀ መግባትም አለባቸው እና በፊቴ ሀትክክል አይደሉምና።
፫ ስለዚህ፣ አገልጋዮቼ ስድኒን እና ፓርሊን፣ ወንጌልን እንድትሰብኩላቸው እሰዳችኋለሁ።
፬ ከእነርሱ በተቀበላቸው ሳይሆን፣ በእናንተ በአገልጋዮቼ በኩል ሀበሚማራቸው በኩል እነርሱን በሚገባ እንዲያስረዳ አገልጋዬ ሊመንም ለዚህ ስራ ይሾማል፤ ይህን በማድረግም እባርከዋለሁ፣ አለዚያም አይበለጽግም።
፭ ጌታ እንዲህም ይላል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ እና አንድያ ልጄን ለአለም ሀቤዛነት ወደ አለም ለልኬአለሁ፣ እና እርሱን የሚቀበልው ይድናል፣ እናም እርሱንም ያልተቀበለው ሐይኮነናል ብዬ እደነግጋለሁና—
፮ እናም ሀየሰውን ልጅም የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት፤ እና ሀይሉንም ለበክብሩ ሐቀኝ በኩል ወስዷል፣ እናም አሁንም በሰማያት ነግሷል፣ እናም በምድር ላይ ወርዶ ሁሉንም ጠላቶች ሁሉ ከእግሩ መበታች እስከሚያደርጋቸው ጊዜ ድረስም ይነግሳል፤ እና ይህም ጊዜ ተቃርቧል—
፯ እኔ፣ ጌታ አምላክ፣ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ነገር ግን ሰአቱንና ሀቀኑን የሰማይ መላእክትም ይሁን ሰው የሚያውቅ የለም፣ እስከሚመጣም ድረስ አያውቁትም።
፰ ስለዚህ፣ ለራሴ ካስቀረኋቸው፣ ከማታውቋቸው ሀቅዱሳን ሰዎች በስተቀር፣ ሁሉም ለኃጢአተኞች ስለሆኑ፣ ሁሉም ሰዎች ንስሀ ይገቡ ዘንድ ፍቃዴ ነው።
፱ ስለዚህ፣ እላችኋለሁ ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ዘለአለማዊ ሀቃል ኪዳኔን ለእናንተ ልኬላችኋለሁ።
፲ እናም ቃል የገባሁትን ፈጽሜአለሁ፣ እና የምድር ሀህዝብ ለዚህ ለይሰግዳሉ፤ እናም፣ በራሳቸውም ካላደረጉት፣ በሀይል ሐዝቅ ይላሉ፣ አሁን ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉትም በሀይል ይዋረዳሉና።
፲፩ ስለዚህ፣ በእነዚህ ህዝብ መካከል ሀእንድትሄዱና፣ ስሙ ጴጥሮስ እንደነበረው እንደ ቀደመው ሐዋርያዬ፣ እንዲህም እንድትሏቸው ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፥
፲፪ በመጀመሪያውና በመጨረሻው፣ በምድር ላይ በነበረው፣ እና ተመልሶም በሚመጣው፣ በጌታ ኢየሱስ ስም እመኑ፤
፲፫ በቅዱስ ትእዛዝ መሰረት፣ ለኃጢአቶች ስርየት፣ ሀንስሐ ግቡ እናም በኢየሱስ ክርስቶስም ስም ተጠመቁ፤
፲፬ ይህን የሚያደርጉም በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ሀእጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ለስጦታን ይቀበላሉ።
፲፭ እናም ዳግም፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ጋብቻን ሀየሚከለክል በእግዚአብሔር የተሾመ አይደለም፣ ለጋብቻ ለሰው ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነውና።
፲፮ ስለዚህ፣ ሰው አንዲት ሀሚስት እንድትኖረው ህግ ነው፣ እናም ሁለቱም አንድ ለሥጋ ይሆናሉ፣ እናም ይህም የሆነው ሐምድር የተፈጠረችበትን አላማ ታሟላ ዘንድ ነው፤
፲፯ እናም ምድር ከመፈጠሯ ሀአስቀድሞ ለእንደፍጥረቱ፣ ምድር በተመደበላት የሰው ቁጥርም ትሞላ ዘንድ ነው።
፲፰ እናም ሰውን ሀስጋ እንዳይበላ፣ ከስጋም ለእንዲለይ የሚከለክል በእግዚአብሔር የተሾመ አይደለም፤
፲፱ ስለሆነም፣ የምድር ሀአራዊት እና የሰማይ አዕዋፋት እና በምድር የሚበቅለውም፣ ለሰው ምግብና ልብስ ጥቅም፣ እናም በበቂም እንዲኖረው የተመደበ ነው።
፳ ነገር ግን አንድ ሰው ከሌላው በላይ ሀእንዲኖረው አልተሰጠም፣ ስለዚህም ለአለም በኃጢአት ወድቃለች።
፳፩ ሳያስፈልገው፣ ደምን ሀለሚያፈሰው ወይም ስጋን ለሚያባክነው ሰው፣ ወዮለት።
፳፪ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ ሀየሚመጣው በሴት ወይም በምድር በሚጓዝ ሰው አምሳል አይደለም።
፳፫ ስለዚህ፣ ሀአትታለሉ፣ ነገር ግን ጸንታችሁ ቆዩ፣ ሰማያት የሚንቀጠቀጡበትን፣ እና ምድርም እንደሰካራም የምትንቀጠቀጥበትን እና ወዲህና ወዲያ የምትናወጥበትን፣ እና ለሸለቆዎችም ከፍ ከፍ የሚሉበትን፣ እና ሐተራራዎችም ዝቅ የሚሉበትን፤ ስርጉጥጓጡም ሜዳ የሚሆንበትን ይህንን መጠብቁ—እና ይህ ሁሉ የሚሆነውም መላዕክቱ ሠመለከቱን ሲነፋ ነው።
፳፬ ነገር ግን የጌታ ታላቅ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ሀያዕቆብ በዱር ይበለፅጋል፣ እና ላማናውያንም እንደ ፅጌረዳ ለያብባሉ።
፳፭ ፅዮንም ሀበኮረብታዎች ላይ ለትበለፅጋለች እናም በተራራዎችም ላይ ሀሴትን ታደርጋለች፣ እናም በመረጥኩትም ስፍራ ላይ አብራ ትሰበሰባለች።
፳፮ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ እንዳዘዝኳችሁ ሂዱ፤ ለኃጢአታችሁ ሁሉ ንስሀ ግቡ፤ ሀለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።
፳፯ እነሆ፣ ከፊታችሁ እሄዳለሁ እናም ሀእከተላችኋለሁ፤ እና ለበመካከላችሁ እሆናለሁ፣ እና እናንተም ሐአታፍሩም።
፳፰ እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ፣ ሀበቶሎም እመጣለሁኝ። እንዲህም ይሁን። አሜን።