ክፍል ፸፮
በየካቲት ፲፮፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ከዚህ ራዕይ ጽሑፉ አስቀድሞ፣ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፥ “ከአምኸርስት ጉባኤ እንደተመለስኩ፣ ቅዱሳን መጻህፍትን መተርጎምን ቀጠልኩ። ከተቀበልኳቸው ከተለያዩ ራዕዮች፣ የሰውን ልጅ ደህንነት የሚመለከቱ ብዙ አስፈላጊ ነጥቦች ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተወሰዱ፣ ወይም ከመከማቸቱ በፊት እንደጠፉ ግልፅ ነበር። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ በስጋ ባከናወነው በኩል ደመወዙን የሚሰጥ ከሆነ፣ ለቅዱሳን የዘለአለም ቤት እንዲሆን የተወሰነበት ሰማይ ከአንድ በላይ የሆኑ መንግስታትን እንደሚያጠቃልል ቀሪው እውነት በራሱ የሚያስረዳ ነው። በዚህም መሰረት፣… የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ስንተረጉም፣ እኔ እና ሽማግሌ ሪግደን የሚቀጥለውን ራዕይ ተመለከትን።” ራዕዩ በተሰጠበት ግዜ፣ ነቢዩ ዮሐንስ ፭፥፳፱ን እየተረጎመ ነበር።
፩–፬፣ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ፭–፲፣ የመንግስት ሚስጥራት ለታማኞቹ ሁሉ ይገለጣሉ፤ ፲፩–፲፯፣ ሁሉም በጻድቃንም ሆነ በኃጢአተኛ ትንሳኤ ከሞት ይነሳሉ፤ ፲፰–፳፬፣ የብዙ አለማት ኗሪዎች በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአት ክፍያ አማካይነት የእግዚአብሔር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ናቸው፤ ፳፭–፳፱፣ የእግዚአብሔር መልአክ ተጣለ እናም ዲያብሎስም ሆነ፤ ፴–፵፱፣ የጥፋት ልጆችም በዘለአለም እርግማን ይሰቃያሉ፤ ሌሎች ሁሉም የተወሰነ የደህንነትን ደረጃ ያገኛሉ፤ ፶–፸፣ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ዘለአለማዊ ክብር ያላቸው ፍጡራን ክብር እና ደመወዝ ተገልጿል፤ ፸፩–፹፣ የተረስትሪያልን መንግስት የሚወርሱትም ተገልጸዋል፤ ፹፩–፻፲፫፣ በቲለስቲያል፣ ተረስትሪያል፣ እና በሰለስቲያል ክብሮች ውስጥ ያሉት ሁኔታቸው ተገልጿዋል፤ ፻፲፬–፻፲፱፣ ታማኝ የሆኑት የእግዚአብሔርን መንግስት ሚስጥራት በመንፈስ ቅዱስ ሀይል አማካይነት ማየት እና መረዳት ይችላሉ።
፩ ሀአድምጡ፣ እናንት ሰማያት ሆይ፣ ምድር ሆይ ጆሮሽን ስጪ፣ እናም ነዋሪዎችዋም ተደሰቱ፣ ጌታ ለእግዚአብሔር ነውና፣ እናም ከእርሱም በቀር ሐማንም መአዳኝ የለምና።
፪ ጥበቡ ሀታላቅ ነው፣ መንገዶቹም ለድንቅ ናቸው፣ እናም የአሰራሩንም መጠን ማንም ሊያገኘው አይቻለውም።
፫ ሀአላማዎቹ አይወድቁም፣ እጁንም ይከለክል ዘንድ የሚቻለው ማንም የለም።
፬ ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ሀአንድ ነው፣ እና አመታቱም ከቶ ለአያልቁም።
፭ ጌታ እንዲህ ይላል—እኔ ጌታ ሀለሚፈሩኝ ለመሀሪ እና ይቅር ባይ ነኝ፣ እና በፅድቅ እና በእውነት እስከ መጨረሻው ሐየሚያገለግሉኝንም በማክበር እደሰታለሁ።
፮ ዋጋቸውም ታላቅ እና ሀክብራቸውም ዘለአለማዊ ይሆናል።
፯ እና ለእነርሱም ሁሉንም ሀሚስጥራት፣ አዎን፣ ከጥንት ጀምሮ የተሰወሩትን የመንግስቴን ሚስጥራት ሁሉ ለእገልጽላቸዋለሁ፣ እና በሚመጡት ዘመናትም መንግስቴን የተመለከቱትን ነገሮች ሁሉ በጎ ፈቃዴን ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።
፰ አዎን፣ የዘለአለምን ድንቆችንም ያውቃሉ፣ የሚመጡትን፣ እንዲሁም የብዙ ትውልዶች ነገሮችንም አሳያቸዋለሁ።
፱ እናም ሀጥበባቸውም ታላቅ ይሆናል፣ እናም ለመረዳታቸውም እስከ ሰማያት የዘለቀ ይሆናል፤ እናም የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለችና፣ እናም የአስተዋዮችም ሐማስተዋል ትሰወራለች።
፲ ሀበመንፈሴም ለአብራላቸዋለሁና፣ እናም የፈቃዴን ሚስጥራት—አዎን እንዲሁም ሐዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን፣ በሰውም ልብ ያልታሰቡትንም ነገሮች፣ መበሀይሌ አሳውቃቸዋለሁ።
፲፩ እኛ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ስድኒ ሪግደን፣ በጌታችን አንድ ሺ ስምንት መቶ ሰላሳ ሁለት አመት በየካቲት አስራ ስድስት ቀን ሀበመንፈስ ሆነን—
፲፪ ሀበመንፈስ ሀይልም፣ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለማየት እና ለመረዳት፣ ለአይኖቻችን ተከፈቱ እናም እውቀቶቻችንም ብሩህ ሆኑ—
፲፫ እንዲሁም አለም ከመፈጠሯ በፊት ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበሩት ነገሮችም፣ በአብ እቅፍ ውስጥ በነበረው በአንድያ ልጁ በኩል፣ ሀከመጀመሪያው ጀምሮ፣ በአብ ተቀድሰው የነበሩትም፤
፲፬ ስለ እርሱም ምስክርን እንሰጣለን፤ እናም የምንመሰክረውም፣ ልጅ ስለሆነው፣ ያየነው እናም በሰማያዊ ሀራዕይ ለስላነጋገርነው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ ወንጌል ነው።
፲፭ ጌታ የሰጠንን ሀየትርጉም ስራ እየሰራን እያለ፣ እንደሚከተለው ወደ ተሰጠን ወደ ዮሐንስ መፅሐፍ በአምስተኛው ምዕራፍ ቁጥር ሀያ ዘጠኝ ላይ ደረስን—
፲፮ ስለ ሙታን ትንሳኤ፣ እነዚያ ሀየሰው ልጅ ድምፅ ለስለ ሚሰሙት በመናገር፥
፲፯ ሀመልካምም ያደረጉ ለጻድቃን ሐትንሣኤ፣ ክፉትንም ያደረጉ በኃጥአን ትንሣኤ ይነሳሉ።
፲፰ አሁን ይህም እንድንደነቅ አደረገን፣ ምክንያቱም በመንፈስ ለእኛ ተሰጥቶን ነበርና።
፲፱ እናም በእነዚህ ነገሮች ላይ ሀእያሰላሰልን ሳለን፣ ጌታ የመረዳት አይኖቻችንን ነካ እናም ተከፈቱ፣ እናም የጌታ ክብርም በዙሪያችን በራ።
፳ እናም የወልድን ሀክብር፣ ለበአብ ሐቀኝ በኩል ተመለከትን እናም እርሱን በሙላት ተቀበልን፤
፳፩ እናም ቅዱሳን ሀመላእክት፣ እና በዙፋኑ ፊት ለተቀድሰው የነበሩትን፣ እግዚአብሔርን ሲያመልኩት እና እርሱንም ለዘለአለም ሐየሚያመልከውን በጉን አየን።
፳፪ እናም አሁን፣ ስለ እርሱ ከተሰጡት ብዙ ሀምስክሮች በኋላ፣ ይህም በመጨረሻ ስለ እርሱ የምንሰጠው ምስክርነት፥ እርሱ ለህያው መሆኑን ነው!
፳፫ ሀበእግዚአብሔር ቀኝ ለአይተነዋልና፤ እናም እርሱ የአብ ሐአንድያ ልጅ እንደሆነም ሲመሰክርም ድምፅ ሰምተናል—
፳፬ ሀአለማትም ለበእርሱ፣ እናም በእርሱም አማካይነት፣ እናም ከእርሱም ዘንድ ናቸው እናም ተፈጥረዋል፣ እናም ነዋሪዎችዋም የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ሐልጆች ናቸው።
፳፭ እናም ይህንም አየን፣ እንመሰክራለንም፣ በእግዚአብሔር ፊት ስልጣን የነበረው፣ አብ ይወደው የነበረው እና በአብም እቅፍ የነበረው በአንድያ ልጁ ያመጸው፣ የእግዚአብሔር ሀመልአክ ከእግዚአብሔር እና ከወልድ ፊት ተጥሎ ነበር፣
፳፮ እና የጥፋት ልጅ ተብሎም ተጠራ፣ ሰማያትም ስለእርሱ አነቡ—እርሱም ሀሉሲፈር፣ የንጋት ልጅ ነበር።
፳፯ እናም የንጋት ልጅ የሆነው እርሱም ሀየወደቀ ነው፣ ወድቋልም፣ ይህንንም ተመለከትን፣ እናም አስተዋልን!
፳፰ እናም በመንፈስ እያለን፣ ጌታ ራዕይን እንድንፅፍ አዘዘን፤ ሰይጣንን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ላይ ሀያመጸውን፣ እና የእግዚአብሔርንና የእርሱን ክርስቶስ መንግስት ለመውሰድ የሻውን የቀደመውን ለእባብ ሐዲያብሎስ አይተነዋልና—
፳፱ እነሆ፣ ከእግዚአብሔር ቅዱሳን ጋርም ሀተዋጋ፣ እናም በዙሪያቸውም ከበባቸው።
፴ እናም በራዕይም የተዋጋቸውን እና ያሸነፋቸውን ስቃይ ተመለከትን፣ እንደህም ሲል የጌታ ድምፅ ወደ እኛ መጣ፥
፴፩ ጌታም ሀይሌን ስለሚያውቁት ሁሉ፣ እናም በዚህም ተካፋይ ስለሆኑት፣ እናም በዲያብሎስም ሀይል አማካይነት ራሳቸውን ሀእንዲሸነፉ እውነትንም እንዲክዱና ሀይሌም እንዲረክስ የፈቀዱትን በተመለከተ እንዲህ ይላል—
፴፪ ባይወለዱ ይሻላቸው ብዬ ያልኳቸው፣ ሀየጥፋት ለልጆች እነርሱ ናቸው፤
፴፫ ከዲያብሎስ እና ከመላእክቱ ጋር ለዘለአለም በእግዚአብሔር ቁጣ ለመሰቃየት የተረገሙ የቁጣ እቃዎች ናቸውና፤
፴፬ እነርሱን በተመለከተ በዚህም አለም ይሁን በሚመጣው አለም ሀይቅርታ የላቸውም ብያለሁ—
፴፭ ከተቀበሉት በኋላ መንፈስ ቅዱስን፣ እና የአብን አንድያ ልጅ ሀስለካዱት፣ እናም እርሱንም በራሳቸው ለስለሰቀሉት እና ስላዋረዱት ይቅርታ የላቸውም።
፴፮ እነዚህም፣ ከዲያብሎስ እና ከመላእክቱ ጋር ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ሀባሕር የሚሄዱት ናቸው—
፴፯ እናም ሁለተኛው ሀሞትም ሀይልን የሚያገኝባቸውም እነርሱ ናቸው፤
፴፰ አዎን፣ በእውነትም፣ ከቁጣው ስቃይ በኋላ፣ በጌታ ዘመንም የማይድኑት እነርሱ ሀብቻ ናቸው።
፴፱ ሌሎቹም ሁሉ፣ በታረደው፣ አለማትም ከመሰራታቸው አስቀድሞ በአብ እቅፍ በነበረው ሀበበጉ ታላቅ ድል እና ክብር የተነሳ፣ በሙታን ለትንሳኤ ሐይመጣሉ።
፵ እና ይህም የሰማያት ድምፅ ለእኛ የመሰከረልን ምስራች ሀወንጌል ነው—
፵፩ እርሱም፣ እንዲሁም ኢየሱስ፣ ለአለም ሀሊሰቀልና ለየአለም ኃጢአቶችን ሐሊሸከም፣ እናም አለምንም መሊቀድስና፣ ከርኩሳትም ሠሊያጸዳ ወደ አለም እንደመጣ፣ የሰማያት ድምፅ የመሰከረልን ምስራች ይህ ነው፤
፵፪ በእርሱም አማካይነት አብ በእርሱ ሀይል ያደረጋቸውን እና በእርሱ የተሰሩት ሁሉ ሀይድኑ ዘንድ፤
፵፫ እርሱም አብን የሚያከብር፣ እናም አብም ከገለጠው በኋላ ወልድን ከሚክዱት የጥፋት ልጆች በስተቀር የእጆቹን ስራዎች ሁሉ የሚያድን ነው።
፵፬ ስለዚህ፣ ከእነርሱም በስተቀር ሁሉን ያድናል—እነርሱም መጨረሻ ወደሌለው፣ ሀየዘለአለም ለቅጣት ወደሆነው፣ ሐከዲያብሎስ እና ከመላእክቱ ጋር ገዢ ለመሆን ስቃያቸው የሆነው መትላቸው ወደ ማይሞትበት እሳቱም ወደ ማይጠፋበት ወደ ዘለአለም ቅጣት ይሄዳሉ—
፵፭ እናም ሀመጨረሻውን፣ ወይም ስፍራውን፣ ወይም ስቃያቸውን ማንም ሰው አያውቅም፤
፵፮ ይህም አልተገለጠም፣ ወይም የዚህ ተካፋዮች ከሆኑት በስተቀር፣ ይህም የተገለጠም አይደለም፣ ወይም ለሰውም አይገለጠም፤
፵፯ ይሁን እንጂ፣ እኔ ጌታ ይህን በራዕይ ለብዙዎች አሳይቻለሁ፣ ነገር ግን ወዲያውም ደግሜ ዘግቼዋለሁ።
፵፰ ስለዚህ፣ የዚህን መጨረሻ፣ ስፋት፣ ከፍታ፣ ሀጥልቀት፣ እና ስቃይ አልተረዱትም፣ ወይም በዚህ ለፍርድ ሐከተመደቡት በስተቀር ማንም ሰው አይረዳውም።
፵፱ እናም ድምፅም እንዲህ ሲል ሰማን፥ ይህን ራዕይ ጻፍ፣ የኃጢአተኞችም ስቃይ መጨረሻ ይህ ነውና።
፶ ደግሞም እንመሰክራለን—አይተን ሰምተናልና፣ እናም ይህም መልካምን በማድረግ በጻድቃት ሀትንሣኤ የሚነሱትን በሚመለከት የክርስቶስ ወንጌል ለምስክርነት ይህ ነው—
፶፩ እነርሱም የኢየሱስን ምስክር የተቀበሉ፣ እናም በስሙም ሀያመኑ እና ቀብሩን በሚመስል ለድርጊት፣ በስሙ በውሀ ውስጥ ሐበመቀበር መየተጠመቁ ናቸው፣ እና ይህንም ያደረጉት እርሱ በሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት ነው—
፶፪ ይህም ትእዛዛትን በማክበርም ከኃጢአታቸው ሁሉ ሀእንዲታጠቡ እና ለእንዲጸዱ፣ እናም ወደዚህ ሐሀይል መበተሾመው እና በተሳሰረው ሠእጆችንም በመጫን መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ነው፤
፶፫ እናም በእምነት ያሸነፉም፣ እናም መልካም ለሚያደርጉት እና ለእውነተኞች ሁሉ አብ በሚያፈሰው ሀበቅዱሱ የተስፋ መንፈስ ለታትመዋል።
፶፬ እነርሱም ሀየበኩር ልጅ ቤተክርስቲያን ናቸው።
፶፭ እነርሱም አብ ሀሁሉንም ነገሮች በእጆቻቸው የሰጣቸው ናቸው—
፶፮ እነርሱም የእርሱን ሙላት እና ክብር የተቀበሉ ሀካህናት እና ነገስታት ናቸው፤
፶፯ እናም ከአንድያ ልጅ ሀስርዓት እና ለየሔኖክ ስርዓት ከነበረው እንደ መልከ ጼዴቅ ስርዓት የልዑልም ሐካህናት ናቸው።
፶፰ ስለዚህ፣ እንደተጻፈውም፣ እነርሱ ሀአማልክቶች፣ እነሆ ለየእግዚአብሔር ሐልጆች ናቸው፣
፶፱ ስለዚህ፣ ሁሉም ነገሮች የእነርሱ ናቸው፣ በህይወትም ይሁን በሞት፣ ወይም አሁን ያሉ ነገሮች ወይም ወደፊት የሚመጡት ነገሮች፣ ሀሁሉም የእነርሱ ናቸውም እነርሱ የክርስቶስ ናቸው፣ እናም ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
፷ እናም እነርሱም ሁሉንም ነገሮች ሀያሸንፋሉ።
፷፩ ስለዚህ፣ ማንም በሰው ሀአይመካ፣ ነገር ግን ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች ለበሚያደርገው በእግዚአብሔር ሐይመካ።
፷፪ እነዚህም በእግዚአብሔር እና በእርሱ ክርስቶስ ሀፊት ለዘለአለም ለይኖራሉ።
፷፫ በምድር በህዝቡ ላይ ሀሊነግስ በሰማይ ደመና ለበሚመጣበት ጊዜ ይዞአቸው የሚመጣውም ሐእነዚህ ናቸው።
፷፬ እነዚህም ሀበመጀመሪያው ትንሳኤ ስፍራም የሚኖራቸውም እነዚህ ናቸው።
፷፭ እነዚህም በጻድቃን ሀትንሳኤ የሚመጡት ናቸው።
፷፮ ወደ ሀፅዮን ለተራራ፣ እናም ከሁሉም በላይ ቅዱስ ወደሆነው ሰማያዊ ስፍራ፣ ወደ ህያው እግዚአብሔር ከተማ የሚመጡትም እነዚህ ናቸው።
፷፯ እነዚህም ወደ አእላፋት መላእክት፣ ወደ ሀሔኖክ እና ወደ ለበኩራት ቤተክርስቲያንና ወደ ታላቁ ጉባኤ የመጡት ናቸው።
፷፰ እነዚህም እግዚአብሔር እና ክርስቶስ ሁሉንም ሀበሚፈርዱበት በሰማይ ስሞቻቸው ለየተጻፉላቸውም ናቸው።
፷፱ እነዚህ ሀየአዲስ ኪዳን አማላጅ በሆነው፣ ይህን ፍጹም ለየኃጢአት ክፍያን በመፈጸም የራሱን ሐደም በማፍሰስ ባከናወነው በኢየሱስ መፍጹም የሆኑት ጻድቃን ሠሰዎች ናቸው።
፸ እነዚህ ሰውነታቸው ሀሰለስቲያል የሆኑ ናቸው፣ ለክብራቸውም እንደ ሐጸሀይ፣ እንዲሁም ከሁሉም በላይ በሆነ የእግዚአብሔር ክብር፣ ክብሩም የጠፈር ጸሀይ አይነተኛ ሆኖ እንደተጻፈ የሆነው ነው።
፸፩ እና ደግሞም፣ ሀየተረስትሪያልን አለም አየን፣ እና እነሆ እናም አስተውሉ፣ እነዚህም የተረስትሪያል የሆኑ፣ ለጨረቃ ከጠፈር ጸሀይ እንደሚለይ፣ ክብራቸው የአብን ሙላት ከተቀበለው የበኩር ቤተክርስቲያን የተለዩ ናቸው።
፸፪ እነሆ፣ እነዚህም ሀካለህግ የሞቱት ናቸው፤
፸፫ እና እነርሱ ደግሞም እንደ ሰዎች በሥጋ ይፈረድባቸው ዘንድ ወልድ የጎበኛቸው፣ እናም ሀወንጌሉንም ለየሰበከላቸው ሐበወኀኒ ውስጥ የነበሩ የሰዎች መነፍሳት ናቸው፤
፸፬ በስጋ የኢየሱስን ሀምስክር ያልተቀበሉ፣ ነገር ግን በኋላ የተቀበሉት ናቸው።
፸፭ እነዚህ በምድር የተከበሩ፣ በሰዎች ተንኮል ምክንያት የታወሩ ሰዎች ናቸው።
፸፮ እነርሱ ክብሩን ቢቀበሉም፣ ሙላቱን ግን የማይቀበሉ ናቸው።
፸፯ እነዚህ የወልድን መገኘት ቢቀበሉም፣ የአብን ሙላት የማይቀበሉ ናቸው።
፸፰ ስለዚህ፣ ሀየተረስትሪያል ሰውነቶች እንጂ የሰለስቲያል ሰውነቶች አይደሉምና፣ እናም ጨረቃ ከጸሀይ ልዩ እንደሆነም ክብሩም እንዲሁ ልዩ ነው።
፸፱ እነዚህም በኢየሱስ ምስክርነት ሀደፋር ያልሆኑት ናቸው፤ ስለዚህ፣ የአምላካችንን መንግስት አክሊል አይቀበሉም።
፹ እናም አሁን ይህም በመንፈስ እያለን ጌታ እንድንፅፈው ያዘዘን ስለ ተረስትሪያል ያየነው ራዕይ መጨረሻ ነው።
፹፩ እና ደግሞም፣ እንዲሁም በጠፈር ውስጥ የኮኮብ ክብር ከጨረቃ ክብር ልዩ እንደሆነ፣ አነስተኛ የሆነውን ሀየቲለስቲያልን ክብር ተመለከትን።
፹፪ እነዚህም የክርስቶስን ወንጌል ወይም የኢየሱስን ሀምስክርነት ያልተቀበሉት ናቸው።
፹፫ እነዚህም መንፈስ ቅዱስን ያልካዱት ናቸው።
፹፬ እነዚህም ወደ ሀሲኦል የተጣሉት ናቸው።
፹፭ እነዚህ ሀእስከመጨረሻው ትንሳኤ ድረስ፣ ጌታ እንዲሁም ክርስቶስ፣ ለበጉ፣ ስራውን እስከሚጨርስ ድረስ ሐከዲያብሎስ ነጻ የማይሆኑት ናቸው።
፹፮ እነዚህም ዘለአለማዊ በሆነው አለም ውስጥ የእርሱን ሙላት የማይቀበሉ፣ ነገር ግን በተረስትሪያል አገልግሎት አማካይነት የመንፈስ ቅዱስን ሙላት የሚቀበሉት ናቸው፤
፹፯ እናም ተረስትሪያልም በሰለስቲያል ሀአገልግሎት አማካይነት ይቀበላሉ።
፹፰ እና ደግሞ የቲለስቲያልም እንዲያገለግሉአቸው በተመረጡት መላእክት ወይም ለእነርሱ አገልጋይ መናፍስት እንዲሆኑ በተመረጡ ይህን ይቀበላሉ፤ እነርሱም የደህንነት ወራሾች ይሆናሉና።
፹፱ እናም በሰማያዊ ራዕይ አዕምሮን ሁሉ የሚያልፈውን የቲለስቲያል ክብርን እንደዚህም ተመለከትን፤
፺ እና እግዚአብሔር ከገለጠለት በስተቀር ማንም አያውቀውም።
፺፩ እናም ከቲለስቲያል ክብር በሁሉም ነገሮች፣ እንዲሁም በክብር፣ በሀይል፣ እናም በስልጣን፣ እናም በአለቅነት የላቀውን የተረስትሪያል ክብርን እንዲህ ተመለከትን።
፺፪ እናም ከሁሉም ነገሮች በላይ የሆነውን፣ እግዚአብሔር፣ እንዲሁም አብ፣ በዙፋኑ ላይ ለዘለአለም የሚነግስበትን የሰለስቲያል ክብርን እንዲህ ተመለከትን፤
፺፫ በዙፋኑ ፊትም ሁሉም ነገሮች በትህትና ሀበማወደስ ይሰግዳሉ፣ እናም ለእርሱም ለዘለአለም ክብርን ይሰጣሉ።
፺፬ በእርሱ ሀፊት የሚኖሩትም ለየበኩር ቤተክርስቲያን ናቸው፤ እናም የእርሱን ሙላት እና ሐጸጋ በመቀበልም እንደሚታዩም ያያሉ፣ እናም መእንደሚታወቁም ያውቃሉ፤
፺፭ እና በሀይልም፣ እና በስልጣን፣ እና በአለቅነትም ሀእኩል ያደርጋቸዋል።
፺፮ እና ሀየጸሀይ ክብር አንድ እንደሆነ የሰለስቲያል ክብርም አንድ ነው።
፺፯ እናም የጨረቃ ክብር አንድ እንደሆነም፣ የተረስትሪያል ክብር አንድ ነው።
፺፰ እናም የከዋክብት ክብር አንድ እንደሆን፣ እንዲሁ የቲለስቲያል ክብር አንድ ነው፤ አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ በክብር እንደሚለይም፣ በቲለስቲያል ክብር ውስጥ በክብር አንዱ ከሌላው የተለየ ነው፤
፺፱ እነዚህም ሀየጳውሎስ፣ እናም የአጵሎስ፣ እናም የኬፋ ናቸው።
፻ እነዚህም የአንድ እና የሌላም—አንዳንዶች የክርስቶስ እና አንዳንዶች ዮሐንስ፣ እናም አንዳንዶቹም የሙሴ፣ እናም አንዳንድ የኤልያስ፣ እናም አንዳንዱ የኢሳይያስ፣ አንዳንዱ የኢሳይያስ፣ እናም አንዳንዱ የሔኖኮች ነን የሚሉ ናቸው፤
፻፩ ነገር ግን ወንጌሉን፣ ወይም የኢየሱስን ወይም የነቢያትን ምስክርነት፣ ወይም ሀየዘለአለም ቃል ኪዳንን ያልተቀበሉ ናቸው።
፻፪ በመጨረሻም፣ እነዚህም ከቅዱሳኑ ጋር፣ ወደ በኩር ሀቤተክርስቲያን በደመና ለእንዲነጠቁ የማይሰበሰቡት ናቸው።
፻፫ ሀእነዚህም ለሀሰተኞች፣ እና አስማተኞች፣ እና ሴሰኞች፣ እና ሐአመንዝሮች፣ እና ሀሰትንም የሚወዱ እና የሚያደርጉትም ናቸው።
፻፬ እነዚህ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን ሀቁጣ የሚቀበሉት ናቸው።
፻፭ እነዚህ፣ ዘለአለማዊ እሳት የቂም ሀበቀልን የሚቀጡትም ናቸው።
፻፮ እነዚህ ወደ ሀሲኦል የሚጣሉት እናም፣ ክርስቶስ ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች ለእስከሚያደርግበት፣ እና ስራውን ሐፍጹም እስከሚያደርግበት እስከ መዘመኑ ፍጻሜ፣ ሠሁሉን በሚገዛው እግዚአብሔር ብርቱ ረቁጣም የሚሰቃዩት ናቸው፤
፻፯ አሸንፌአለሁ እናም መጥመቂያው፣ እንዲሁም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ሀወይን መጥመቂያን፣ ብቻዬን ለረግጫለሁ፣ በማለት መንግስትን ወደ አብ በፍጹም ንፅህና እንከሚያስረክብበት ድረስ የሚሰቃዩት እነርሱ ናቸው።
፻፰ ከዚያም እርሱም በስልጣኑ ሀዙፋኑ ለዘለአለም ይነግስ ዘንድ የክብር አክሊል ይጫንለታል።
፻፱ ነገር ግን እነሆ፣ እናም አስተዋሉ፣ የቲለስቲያል አለምን ክብር እና ኗሪዎችን፣ በሰማይ ጠፈር እንዳሉት ከዋክብት አይነት፣ ወይም እንደ ባህር ዳር አሸዋዎች ለመቆጠር እንደማይቻሉም አየን።
፻፲ እናም የጌታ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማን፥ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጠው ከዘለአለም እስከ ዘለአለም እነዚህ ሁሉ በጉልበት ይንበረከካሉ፣ እናም እያንዳንዱ ምላስም ሀይናዘዝለታል፤
፻፲፩ እንደ ስራቸውም መጠን ይፈረድባቸዋል፣ እናም ለእያንዳንዱ ሰውም ሀእንደስራው በተዘጋጀለት ለመኖሪያ ግዛቱን ይቀበላል፤
፻፲፪ እና እነርሱም የልዑል አገልጋዮች ይሆናሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር እና ክርስቶስ ሀበሚኖሩበት፣ ከዘለአለም እስከዘለአለም መምጣት አይችሉም።
፻፲፫ ይህም በመንፈስ ሳለን ያየነውና እንድንፅፈውም የታዘዝነው ራዕይ መጨረሻ ነው።
፻፲፬ ነገር ግን የጌታ ስራዎች፣ እናም በክብርና፣ በሀይል፣ እናም በአለቅነት ለማስተዋል ከሚቻለው በላይ እንደሆኑ ያሳየን የመንግስቱ ሀሚስጥራት ለታላቅና አስደናቂ ናቸው፤
፻፲፭ እነዚህንም በመንፈስ እያለንም እንዳንፅፋቸው አዝዞናል፣ እናም ሰው ይናገራቸው ዘንድ ሀበህግ ያልተገቡ ናቸው።
፻፲፮ ሰው ያሳውቃቸው ዘንድ ሀችሎታ አይኖረውም፣ እግዚአብሔር ለሚወዱት እና በፊቱም ራሳቸውን ለሚያጸዱት በሚሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ብቻ ሰው ሊያያቸው እና ለሊረዳቸው ይቻለዋልና፤
፻፲፯ ለእነዚህም ራሳቸው የሚያዩበትን እና የሚያውቁበትን ልዩ መብት ይሰጣቸዋል፤
፻፲፰ በስጋ እያሉም፣ በመንፈስ ሀይል እና በመገለጥ በኩል በክብር አለም ውስጥ የእርሱን መገኘት ያዩ ዘንድም ይሰጣቸዋል።
፻፲፱ እናም ለእግዚአብሔር እና ለበጉ ክብር እና ውዳሴ፣ እናም አለቅነትም ከዘለአለም እስከዘለአለም ይሁን። አሜን።