ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች
ክፍል ፩
በህዳር ፩፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ልዮ ጉባዔ ወቅት በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የተሰጠ ራዕይ። ከዚህ ጊዜ ቀደም ብሎ ብዙ ራእዮች ከጌታ ተሰጥተው ነበር፣ እናም እነዚህ ራዕዮች በመጽሐፍ መልክ ተጠርዘው እንዲታተሙ በጉባኤው ውሳኔ ከተሰጠባቸው ዋነኛ ሐሳቦች መካከል አንዱ ነበር። ይህ ክፍል በዚህ ዘመን የተሰጡትን ትምህርቶች፣ ቃልኪዳኖች፣ እና ትዛዛትን በተመለከተ የጌታን መግቢያ የያዘ ነው።
፩–፯፣ የማስጠንቀቂያው ድምጽ ለሁሉም ሰው ነው፤ ፰–፲፮፣ ክህደትና ክፋት ዳግም ምፅዓትን ይቀድማሉ፤ ፲፯–፳፫፣ ጆሴፍ ስሚዝ የጌታን እውነት እና ሀይል በምድር ዳግመኛ እንዲመልስ ተጠርቷል፤ ፳፬–፴፫፣ መፅሐፈ ሞርሞን መጥቷል እናም እውነተኛ ቤተክርስቲያን ተመስርታለች፤ ፴፬–፴፮፣ ሰላምም ከምድር ይወሰዳል፣ ፴፯–፴፱፣ እነዚህን ትዛዛት መርምሩ።
፩ ከፍ ብሎ የሚኖረው እና ሀአይኖቹንም በሁሉም ሰዎች ላይ የሆነው፣ የእርሱ ድምፅ አቤቱ እናንት ለየቤተክርስቲያኔ ሰዎች ሆይ አድምጡ ይላል፣ አዎን እውነት እላለሁ፥ እናንት በሩቅ ያላችሁ፣ በባህር ደሴቶች ላይ ያላችሁ ሐስሙ፣ በአንድነትም አድምጡ።
፪ በእውነት የጌታ ሀድምጽ ለሁሉም ሰው ነውና፣ እናም ለማንም አያመልጥም፤ እናም የማያይ አይንም ሆነ የማይሰማ ጆሮ፣ ወይም የማይጣስ ሐልብ አይኖርም።
፫ እናም ሀአመጸኞች በብዙ ሐዘን ይወጋሉ፤ ኃጢአታቸውም በቤቶች አናት ላይ ለይነገራሉ፣ የሚስጥር ተግባሮቻውም ይገለጣሉ።
፬ እናም ሀበመጨረሻዎቹ ቀናት፣ እኔ በመረጥኳቸው ደቀመዛሙርቶቼ አንደበት፣ የማስጠንቀቂያው ለድምጽ ለሁሉም ህዝብ ይሆናል።
፭ እናም እነርሱም ወደፊት ይሄዳሉ፣ ማንም አያግዳቸውም፣ እኔ ጌታ አዝዣቸዋለሁና።
፮ እነሆ አቤቱ! የምድር ነዋሪዎች፣ ለእናንተ ሀእንዲያሳትሙት የሰጠዋችሁ ይህ የእኔ ለስልጣን፣ እንዲሁም የአገልጋዮቼ ስልጣን፣ እናም ለመፅሐፈ ትእዛዛቴ መቅድም ነው።
፯ ስለዚህ፣ ሀፍሩ እናም ተንቀጥቀጡ፣ አቤቱ! እናንት ሕዝቦች ሆይ፣ እኔ ጌታ በእነርሱ ያወጅኩት ለይፈጸማልና።
፰ እናም እውነት እላችኋለሁ፣ ይህንን የምስራች ይዘው ወደ ምድር ነዋሪዎች የሚሄዱ፣ ለእነርሱ በምድርም ሆነ በሰማይ፣ የማያምኑትን እና ሀአመጸኞችን ለየማሰር ኃይል ተሰጥቷቸዋል፤
፱ አዎን፣ እውነት፣ የእግዚአብሔር ሀቁጣ ለበክፉዎች ላይ ያለልክ የሚወርድበት ቀን እስከሚመጣ ድረስ እንዲያስሯቸው—
፲ ጌታ መጥቶ ለእያንዳንዱን ሰው ሀእንደየስራው ለመጠን ሐእስኪመልስ እና ሁሉም ሰው ለባልንጀራው በሰፈረበት መጠን እስከሚሰፍርበት መቀን ድረስ የማሰር ኃይል ተሰጥቷቸዋል።
፲፩ ስለዚህ የሚሰማ ሁሉ ይሰማ ዘንድ፣ የጌታ ድምጽ እስከ ምድር ዳርቻ ነው፥
፲፪ ለሚመጣው ተዘጋጁ ተዘጋጁ፤ ጌታ ተቃርቧልና፤
፲፫ እናም የጌታ ሀቁጣ ተቀጣጥሏል፣ እናም ለሰይፉም በሰማይ ታጥቧል፣ እንዲሁም በምድር ነዋሪዎችም ላይ ይወርዳል።
፲፬ እናም የጌታ ሀክንድ ይገለጣል፤ የጌታን ድምጽ ሆነ ያገልጋዮቹን ድምጽ ለከማይሰሙ፣ ለነቢያት እና ለኃዋሪያት ቃላት ሐትኩረት ከማይሰጡ ሰዎች መካከል መየሚገለሉበት ቀን ይመጣል፣
፲፭ ሀከስርዓቴ ለእርቀዋል፣ እናም ሐዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን መአፍርሰዋልና፤
፲፮ ጽድቁን ለመመስረት ጌታን ሀአይፈልጉም፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው ለበገዛ ሐመንገዱ፣ እናም ቁሳቁሱ የጣኦት በሆነው፣ መአምሳያውም የአለም በሆነው፣ ሠአርጅቶም ረበባቢሎን በሚጠፋው፣ እንዲሁም በምትወድቀው በታላቂቷ ባቢሎን እንደ አምላኩ ምስል ይጓዛል።
፲፯ ስለዚህም እኔ ጌታ በምድር ሀነዎሪዎች ላይ የሚመጣውን መቅሰፍት በማወቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን ጠራሁት እናም ከሰማይም ተናገርኩት እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጠሁት፤
፲፰ እናም ደግሞ ይህንን የምስራች ለአለም እንዲያውጁ፣ እናም ይህን ሁሉ ያደረኩትም በነቢያቶች የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ለሌሎችም ትእዛዛትን ሰጥቻለሁ—
፲፱ የአለም ሀደካማ ነገሮች ወደፊትም ይወጣሉ ብርቱውን እና ጠንካራውን ይሰብራሉ፣ ሰው ባልጀራውን መምከር አይገባውም፣ በስጋ ክንድ ለመመካት አይኖርበትም—
፳ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የአለም አዳኝ በሆነው በጌታ እግዚአብሔር ስም ሀይናገር ዘንድ፤
፳፩ ደግሞም እምነትም በምድር ይበዛ ዘንድ፤
፳፪ ዘለአለማዊ ሀቃልኪዳኔ ይመሰረት ዘንድ፤
፳፫ ሀየወንጌሌ ሙላት ለበደካሞች እና በተራ ሰዎች አማካይነት በነገስታት እና በገዢዎች ፊት እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሐይታወጅ ዘንድ ተሰጥቷቸዋል።
፳፬ እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ እኔም ተናግሬዋለሁ፤ እነዚህ ሀትእዛዛት ከእኔ ዘንድ ናቸው፣ በድክመታቸው፣ ለእንደቋንቋቸው ወደ ሐመረዳት ይመቱ ዘንድ ለአገልጋዮቼ ተሰጥተዋቸዋል።
፳፭ እናም ስህተትን እስከፈጸሙ ድረስ ስተታቸውን እንዲታወቁ፤
፳፮ እናም ሀጥበብንም እስከፈለጉ ድረስ ያንኑ ይማሩ ዘንድ፤
፳፯ እናም ኃጢአትን እስከሰሩ ድረስ ሀንስሀ እንዲገቡ ለይገሰጹ ዘንድ፤
፳፰ ሀትሁት እስከሆኑ ድረስ እንዲበረቱ እና ከላይም እንዲባረኩ፣ እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለእውቀትንም ይቀበሉ ዘንድ ነው።
፳፱ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊም ቢሆን የኔፋውያንን መዝገብ ከተቀበለ በኋላ፤ አዎን በእግዚአብሔር ምህረት፣ በእግዚአብሔር ኃይል ሀመፅሐፈ ሞርሞንን የመተርጎም ኃይል ይኖረው ዘንድ ነው።
፴ እናም ደግሞ እነዚህ ትእዛዛት የተሰጣቸው በምድር ገጽ ላይ ሁሉ ብቸኛ እውነተኛ እና ህያው የሆነችውን ሀቤተክርስቲያን፣ እኔም ጌታ በጣም ለየተደሰትኩባትን የእዚህችን ሐቤተክርስቲያን መሰረት የመጣል፣ እና መከጭለማ እና ከተደበቀችበት የማውጣት ሠኃይል ይኖራቸው ዘንድ ነው። እነዚህን ነገሮች ለቤትክርስቲያኗ ስናገር በጋራ እንጂ በተናጠል አይደለም—
፴፩ እኔ ጌታ ሀኃጢአትን በዝቅተኛ ደረጃ መመልከት አይቻለኝምና፤
፴፪ ሆኖም፣ ንስሀ የሚገባ እና የጌታን ትእዛዛት የሚጠብቅ ሀይቅርታን ይቀበላል፤
፴፫ እናም ሀንስሀ የማይገባ፣ የተቀበለውም ብርሀን ቢሆን እንኳን ከእርሱ ለይወሰድበታል፤ ሐመንፈሴም ከሰው ጋር ዘወትር መአይሆንምና፣ ይላል የሰራዊት ጌታ።
፴፬ እናም ደግሞ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አቤቱ የምድር ነዋሪዎች ሆይ፥ እኔ ጌታ እነዚህን ነገሮች ለስጋ ለባሽ ሀሁሉ ለማሳወቅ ፍቃደኛ ነኝ፤
፴፭ እኔም ለሰዎች ሀአላደላም፣ እናም ለቀኑ በፍጥነት እንደመጣ ሁሉም ሰው ያውቀው ዘንድ ፍቃዴ ነው፤ ሐሰላም ከምድር የሚወሰድበት፣ እና መዲያብሎስም በግዛቱም ላይ ኃይል የሚያገኝበት ሰዓት አልደረሰም ነገር ግን ተቃርቧል።
፴፮ እናም ደግሞ ጌታ ሀበቅዱሳኑ ላይ ኃይል ይኖረዋል፣ እናም ለበመካከላቸውም ሐይነግሳል እናም መበኢዱሜአ ወይም በአለም ላይ ሠበፍርድ ይወርዳል።
፴፯ እነዚህን ሀትእዛዛት መርምሩ፣ የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና፣ እናም በውስጣቸው ያሉት ትንቢቶች እና ለየተስፋ ቃላት ሁሉ ይፈጸማሉ።
፴፰ እኔ ጌታ የተናገርኩትን፣ ተናግሬያለሁ፣ እናም አላመካኝም፤ ሰማያትና ምድር ቢያልፉም ሀቃሌ ግን አያልፍም፣ ነገር ግን ሁሉም ለይፈጸማል፣ በእኔ ሐድምጽ ሆነ መበአገልጋዮቼ ድምጽ፣ ያም ሠአንድ ነው።
፴፱ ስለሆነም፣ እናም አስተውሉ፣ ጌታ አምላክ ነው፣ ሀመንፈስም ይመሰክራል፣ እናም ምስክርነቱም እውነት ነው፣ እናም ለእውነት ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይኖራል። አሜን።