ክፍል ፳
ስለቤተክርስቲያን አደረጃጀት እና አስተዳደር፣ በፈየት፣ ኒው ዮርክ ወይም በዚያ አካባቢ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። የዚህ ራዕይ ክፍሎች የተሰጡት በበጋ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) አካባቢ ሳይሆን አይቀርም። በዚያ ጊዜ አንቀጾች እና ቃል ኪዳኖች ተብሎ የሚታወቀው ሙሉ ራዕዩ የተመዘገበው በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (ቤተክርስቲያኗ በተደራጀችበት ቀን) ሳይሆን አይቀርም። ነቢዩ እንደጻፈው፥ “በትንቢት እና ራዕይ መንፈስ ከእርሱ [ከኢየሱስ ክርስቶስ] የሚከተለውን ተቀበልን፤ ይህም ብዙ መረጃዎችን ብቻ ሳይሆን የሰጠን፣ ነገር ግን እንደ እርሱ ፈቃድ እና ትእዛዝ መቼ የእርሱን ቤተክርስቲያን ዳግም በምድር ላይ ማቋቋም እንደሚገባን ጠቁሞናል።”
፩–፲፮፣ መፅሐፈ ሞርሞን የኋለኛው ቀን ስራን መለኮታዊነት ያረጋግጣል፤ ፲፯–፳፰፣ የፍጥረት፣ የውድቀት፣ የኃጢአት ክፍያ፣ እናም የጥምቀት ትምህርቶች ተረጋግጠዋል፤ ፳፱–፴፯፣ ንስሀ፣ መፅደቅን፣ ቅድስናን፣ እና ጥምቀትን የሚያስተዳድሩ ህጎች ተገልጸዋል፤ ፴፰–፷፯፣ የሽማግሌዎች፣ የካህናት፣ የመምህራን፣ እናም የዲያቆናት ሀላፊነቶች በአጭር ተጠቃለዋል። ፷፰–፸፬፣ የአባላት ሀላፊነቶች፣ ልጆችን መባረክ፣ እና ጥምቀት የሚከናወንበትም ዘዴዎች ተገልጠዋል፤ ፸፭–፹፬፣ የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች እና የቤተክርስቲያን አባልነትን ማስተዳደሪያ ደንቦች ተሰጥተዋል።
፩ በእነዚህ በኋለኞቹ ቀናት የክርስቶስ ሀቤተክርስቲያን ለመነሳት፣ ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺ ስምንት መቶ ሰላሳ አመት ሲሆን፣ ቤተክርስቲያኗም በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ትእዛዝ ሚያዝያ በሚባለው በአራተኛው ወር በስድስተኛው ቀን ለአገራችን ህግ ዘወትር ተስማሚ በሚሆን ሁኔታ ሐተደራጅታ ተመስርታለች—
፪ እነዚህም ትእዛዛት የተሰጡት በእግዚአብሔር ሀለተጠራው፣ እና የዚህች ቤተክርስቲያን መጀመሪያ ለሽማግሌ በመሆን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐሐዋርያ እንዲሆን ለተሾመው ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ ነበር፤
፫ እናም በእግዚአብሔር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሀዋሪያ፣ የዚህች ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ሽማግሌ እንዲሆን ለተጠራው እና በእርሱ እጅ ለተሾመው ለኦሊቨር ካውድሪ ነው፤
፬ ይህም እንደጌታችን እና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ነው፣ ለእርሱም አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን። አሜን።
፭ ይህ የመጀመሪያው ሽማግሌ የኃጢአት ስርየት እንደተቀበለ በእውነት ከተገለጸለት በኋላ፣ በአለም ከንቱነት ውስጥ ደግሞም ሀተጠላለፈ፤
፮ ነገር ግን ንስሀ ከገባ፣ እናም በእምነት እራሱን በቅንነት ትሑት ካደረገ በኋላ፣ ሀመልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ፣ እናም ልብሱ ከንጣቶች ሁሉ በላይ ንጹ እና ነጭ በነበረው ቅዱስ ለመልአክ በኩል እግዚአብሔርም አገለገለው፤
፯ እና ያነሳሱትን ትዕዛዛትንም ሰጠው፤
፰ እናም መፅሐፈ ሞርሞንን ለመተርጎም ቀደም ብሎ በተዘጋጁት ሀመንገዶች በኩል ከላይ ሀይልን ሰጠው፤
፱ ይህም የወደቁትን ሰዎች መዝገብ፣ እናም ለአህዛብና ለአይሁድ ሁሉ ሀሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ለወንጌል የያዘ ነው፤
፲ በሚያነሳሳ መንፈስ የተሰጠ፣ እናም በመላእክት አገልግሎት ሀለሌሎችም የተረጋገጠ፣ እና በእነርሱም ለአለምም ለየተገለጸ ነው—
፲፩ ይህ ቅዱሳን መጻህፍት ሀእውነት እንደሆነ እናም በዚህ እድሜና ዘመን እንደ ቀደሙት ትውልዶችም እግዚአብሔር የእርሱን ቅዱስ ለስራ እንዲያከናውኑ ሰዎችን ሐእንደሚያነሳሳ እና እንደሚጠራ በማረጋገጥ ነው።
፲፪ በዚህም እርሱ ትላንትናም ዛሬም እናም ለዘለአለም ሀአንድ አይነት አምላክ እንደሆነ በማሳየት ነው። አሜን።
፲፫ ስለዚህም፣ በጣም ታላቅ ምስክርነቶች ስላሏቸው፣ ዓለም ሁሉ፣ እንዲሁም ከዚህ በኋላ ወደዚህ እውቀት የሚመጡት ሁሉ፣ በእነርሱ ይፈረድባቸዋል።
፲፬ እናም በእምነት የሚቀበሉት ሁሉ፣ እናም ሀፅድቅን የሚሰሩ፣ የዘለአለማዊ ህይወት ለአክሊልን ይቀበላሉ፤
፲፭ ነገር ግን ሀባለማመን ልባቸውን የሚያደነድኑ፣ እናም ለሚያስወግዱት፣ ወደ ኩነኔያቸው ይለወጣል—
፲፮ ጌታ እግዚአብሔር ተናግሮታልና፣ እናም እኛ የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች፣ በላይ ያለውን የከበረ ግርማዊ ቃላቶቹን ሰምተናል እናም ምስክርነታችንን እንሰጣለን፣ ለእርሱም ክብር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይሁን። አሜን።
፲፯ በእነዚህ ነገሮች መጨረሻ የሌለውና ዘለአለማዊ የሆነው፣ ሰማይና ምድርን እናም በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረ ከዘለአለም እስከዘለአለም ያው የሆነ የማይቀየር አምላክ ሀእግዚአብሔር በሰማይ ውስጥ እንደሚገኝ ለእናውቃለን፤
፲፰ እርሱም ሰውን፣ ወንድና ሴትን፣ ሀበመልኩ እና በአምሳሉ ለፈጠራቸው፤
፲፱ እናም እውነተኛውን እና ህያው የሆነውን እግዚአብሔርን ብቻ ሀእንዲወዱና ለእንዲያገለግሉ እናም ሐየሚያመልኩት እርሱን ብቻ እንዲሆንም ትእዛዛትን ሰጣቸው።
፳ ነገር ግን እነዚህን ቅዱስ ህጎችን በመተላለፍ ሰው ሀስጋዊና ለአጋንንታዊ ሆነ፣ እናም ሐየወደቀ ሆኑ።
፳፩ ስለዚህ፣ ለእርሱ በሰጠው በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ስለእርሱ እንደተጻፈው፣ ሁሉን የሚገዛው እግዚአብሔር ሀአንድያ ልጁን ሰጠ።
፳፪ እርሱም ሀበፈተናዎች ተሰቃየ ነገር ግን እራሱን አሳልፎ አልሰጠም።
፳፫ እርሱም ሀተሰቀለ፣ ሞተ፣ እናም በሶስተኛውም ቀን ዳግም ከሞት ለተነሳ፤
፳፬ እናም ሀበአብ ቀኝ በኩል ለመቀመጥ፣ እና እንደአብ ፈቃድ በፍጹም ሀይል ለመንገስ ወደሰማይ ለአረገ፤
፳፭ ይህም በእርሱ ቅዱስ ስም ሀአምነው እና ተጠምቀው፣ እናም እስከመጨረሻም ድረስ በእምነት ለየጸኑት ሁሉ ይድኑ ዘንድ ነው—
፳፮ በስጋ ከመጣበት ሀከመካከለኛው ዘመን በኋላ የሚያምኑት ብቻ ሳይሆን፣ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ፣ እንዲሁም ከመምጣቱ አስቀድሞ፣ በመንፈስ ቅዱስ ለስጦታ ተነሳስተው ሐቅዱሳን ነቢያት ስለእርሱ በሁሉም ነገሮች መበመመስከር በተናገሯቸው ቃላት ያመኑት ሁሉ ዘለአለማዊ ህይወትን ያገኛሉ፣
፳፯ ስለአብና ወልድ ሀበሚመሰክረው መንፈስ ቅዱስ በኩል በሚመጡት በእግዚአብሔር ለስጦታዎች እና ጥሪዎች የሚያምኑት ከእርሱ በኋላ የሚመጡትም እንዲሁም ይሆንላቸዋል፤
፳፰ አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ መጨረሻ የሌላቸውና ዘለአለማዊ ሀአንድ አምላክ ናቸው። አሜን።
፳፱ እናም ሁሉም ሰው ሀንስሀ መግባትና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለማመን፣ እናም አብን በእርሱ ስም ማምለክ፣ እናም በስሙ እስከፍጻሜው መጽናት እንዳለባቸው እናውቃለን፣ ወይም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ሐመዳን አይችሉም።
፴ እናም በጌታችንና አዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሀጸጋ በኩል የምናገኘው ለፅድቅ ፍትሀዊ እና እውነተኛ እንደሆነ እናውቃለን፤
፴፩ እናም በጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የሚገኘው ሀቅድስና በሙሉ ለሀይላቸው፣ አዕምሮአቸው፣ እናም ጉልበታቸው እግዚአብሔርን ወድደው ለሚያገለግሉት ሁሉ ትክክል እና እውነተኛ እንደሆነ እናውቃለን።
፴፪ ነገር ግን ሰው ከጸጋ ሀወድቆ ከህያው እግዚአብሔር ለመለየት የሚያስችለው ሁኔታም አለ፤
፴፫ ስለዚህ ሀበፈተና እንዳይወድቁ፣ ቤተክርስቲያኗ ትጠንቀቅ እና በየጊዜውም ትጸልይ፤
፴፬ አዎን፣ እንዲሁም የተቀደሱትም ቢሆኑም እንኳን ይጠንቀቁ።
፴፭ እናም እነዚህ ነገሮች እውነተኛ እና ከዮሐንስ ራዕይ ጋር የሚግባቡ፣ ሀከቅዱስ መጻህፍቶችም፣ ወይም በመንፈስ ቅዱስ ስጦታና ሀይል፣ በእግዚአብሔር ለድምጽ፣ ወይም በመላእክት አገልግሎት በኩል በሚመጡት የእግዚአብሔር ራዕዮች ላይም ሐየማይጨምሩ እና የማይቀንሱ እንደሆኑ እናውቃለን።
፴፮ እናም ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሯል፤ እናም ክብር፣ ሀይል፣ እናም ግርማ ለቅዱስ ስሙ አሁን እናም ለዘለአለም ይሁን። አሜን።
፴፯ ደግሞም፣ የጥምቀትን ስርዓት በተመለከተ ለቤተክርስቲያኗ በትእዛዝ መልክ የተሰጠ—ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ትሁት የሚያደርጉ፣ እናም ሀለመጠመቅ ከፈለጉ እናም ለበተሰበረ ልብ እና በተዋረደ መንፈስ ከመጡ፣ እናም ከቤተክርስቲያኗ ፊት በእውነት ለኃጢአታቸው ሁሉ ንስሀ እንደገቡ ምስክር ካደረጉ፣ እናም እርሱን እስከመጨረሻ ድረስ ለማገልገል ፈቃድ ኖሯቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ሐስም በራሳቸው ለመውሰድ መፈቃደኛ ከሆኑ፣ እናም የኢየሱስ ክርስቶስን መንፈስ ለኃጢአት ሠስርየት እንደተቀበሉ ረበስራቸው በእውነት ካሳዩ፣ ወደ እርሱም ቤተክርስቲያን በጥምቀት ይወሰዳሉ።
፴፰ የሽማግሌዎች፣ የካህናት፣ የመምህራን፣ የዲያቆናት፣ እናም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ሀላፊነት። ሀሐዋርያ ሽማግሌ ነው፣ እናም ለማጥመቅም ለእርሱ የተሰጠ ጥሪ ነው፤
፴፱ እናም ሌሎች ሽማግሌዎችን፣ ካህናትን፣ መምህራንን፣ እናም ዲያቆናትን ሀለመሾም፤
፵ እናም የክርስቶስ ስጋና ደም ምልክቶች የሆኑትን ወይንን እና ዳቦን ሀመባረክ—
፵፩ እና ቅዱሳት መጻህፍቱ እንደሚሉትም፣ ለእሳትና ሀለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ለእጆቻቸውን በመጫን ወደ ቤተክርስቲያኗ የተጠመቁትን ሐማጽናት፤
፵፪ እናም ማስተማር፣ ማብራራት፣ አጥብቆ መምከር፣ ማጥመቅ፣ እናም ቤተክርስቲያኗን መጠበቅ፤
፵፫ እናም እጆችን በመጫን ቤተክርስቲያኗንም ማጽናት፣ እናም መንፈስ ቅዱስንም መስጠት፤
፵፬ እናም በስብሰባዎች ሁሉ መሪነትን መያዝ ነው።
፵፭ ሽማግሌዎችም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝና ራዕይ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስብሰባዎችን ሀማስተዳደር አለባቸው።
፵፮ ሀየካህን ሀላፊነት መስበክ፣ ለማስተማር፣ ማብራራት፣ አጥብቆ መምከር፣ እናም ማጥመቅ፣ እናም ቅዱስ ቁርባንን መባረክ ነው፣
፵፯ እናም የእያንዳንዱን አባል ቤትን መጎብኘት፣ እናም በሚስጥር እና ሀበድምፅ ለእንዲጸልዩ እና ሐየቤተሰብ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ በጥብቅ ማበረታት ነው።
፵፰ ሌሎች ካህናትን፣ መምህራንን፣ እናም ዲያቆናትን ሀመሾምም ይችላል።
፵፱ እናም ሽማግሌ በሌለበትም ጊዜ ስብሰባዎችን ይመራል።
፶ ሽማግሌ ባለበት ጊዜ ግን፣ የእርሱ ተግባር መስበክ፣ ማስተምር፣ ማብራራት፣ አጥብቆ መምከር፣ እናም ማጥምቅ፣
፶፩ እናም የእያንዳንዱን አባል ቤት መጎብኘት፣ እናም በሚስጥር እና ድምጻቸውን አውጥተው እንዲጸልዩ እና የቤተሰብ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ ማበርታት ብቻ ነው።
፶፪ አስፈላጊ ሲሆን ካህን በእነዚህ ሀላፊነቶቹ ሁሉ ሽማግሌውን ሀይረዳል።
፶፫ ሀየመምህሩ ሀላፊነትም ቤተክርስቲያኗን ዘወትር ለመጠበቅ፣ እና እነርሱን መርዳትና ማጠንከር ነው፤
፶፬ እናም ምንም ጥፋት በቤተክርስቲያኗ እንዳይኖር፣ እንዲሁም አባላቶቿ እርስ በራሳቸው ሀእንዳይከፋፉ፣ እንዳይዋሹ፣ እንዳይተማሙ፣ ወይም ለክፉ እንዳይነጋገሩ መጠበቅ፤
፶፭ እናም ቤተክርስቲያንም በየጊዜው እንዲሰበሰቡ ማድረግ፣ እናም አባላቶቿ ሀላፊነታቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ ነው።
፶፮ ሽማግሌ ወይም ካህን በማይኖሩበት ጊዜም የስብሰባውን መሪነት ይወስዳል—
፶፯ እናም አስፈላጊ በሚሆንም ጊዜ፣ በቤተክርስቲያኗ ሀላፊነቶቹ ሁሉ ሀዲያቆናት ይረዱታል።
፶፰ ነገር ግን መምህራንም ሆኑ ዲያቆናት የማጥመቅ፣ ቅዱስ ቁርባንን የመባረክ፣ ወይም እጆችን የመጫን ስልጣን የላቸውም፤
፶፱ ነገር ግን እነርሱ ማስጠንቀቅ፣ ማብራራት፣ ማበረታታት፣ እናም ማስተማር፣ እናም ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ አለባቸው።
፷ እያንዳንዱም ሀሽማግሌ፣ ካህን፣ መምህር፣ ወይም ዲያቆን ከእግዚአብሔር በተሰጠው ስጦታዎች እና ለጥሪዎች መሰረት ይሾም፤ እናም እርሱን በሚሾመው ውስጥ በሚገኝ መንፈስ ቅዱስ ሀይልም ይሾማል።
፷፩ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙት ሽማግሌዎችም በሶስት ወር አንድ ጊዜ፣ ወይም ጉባኤው እንደሚመራውና እንደሚቀጥረው በጉባኤ ይሰብሰቡ፤
፷፪ እናም ይህም ጉባዔ በወቅቱ መሰራት ያለባቸውን ማንኛውም የቤተክርስቲያኗን ስራ መስራት አለበት።
፷፫ ሽማግሌዎች አባል ከሆኑበት ቤተክርስቲያን ወይም ከጉባዔው ሀበምርጫ አማካይነት ከሌሎች ሽማግሌዎች ፈቃዳቸውን ይቀበሉ።
፷፬ በካህን የተሾመው እያንዳንዱም ካህን፣ መምህር፣ ወይም ዲያቆንም ሀየምስክር ወረቀት በተሾመበት ጊዜ ከካህኑ መውሰድ ይችላል፣ ይህም የምስክር ወረቀት ለሽማግሌው በሚያቀርብ የጥሪውን ሀላፊነት ለማከናወን የሚያስችለው ስልጣን ይሰጠዋል፣ ወይም ይህን ከጉባኤ ሊቀበለው ይችላል።
፷፭ የዚህ ቤተክርስቲያን ቅርንጫፍ በተደራጀበት ስፍራ፣ ያለቤተክርስቲያኗ ሀምርጫ ማንም ሰው በቤተክርስቲያን ሀላፊነት ለአይሾምም፤
፷፮ ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ ቅርንጫፍ ባለመኖሩ ምርጫ ሊጠራ በማይቻልበት ስፍራ፣ የሽማግሌዎች አመራር፣ ተጓዥ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ከፍተኛ አማካሪዎች፣ ሊቀ ካህናት፣ እና ሽማግሌዎች የመሾም መብት ሊኖራቸው ይችላል።
፷፯ እያንዳንዱ የታላቅ ክህነት ፕሬዘደንት (ወይም የካህናት አመራር)፣ ሀኤጲስ ቆጶስ፣ ከፍተኛ አማካሪ፣ እናም ለሊቀ ካህናት ሐበከፍተኛ ሸንጎ ወይም በአጠቃላይ ጉባኤ አመራር መሾም አለበት።
፷፰ አባላት ከተጠመቁ በኋላ ያለባቸው ሀሀላፊነት—ለቅዱስ ቁርባኑን ከመውሰዳቸውና ሽማግሌዎች ሐእጆቻቸውን በመጫን ከሚያጸኗቸው በፊት፣ ሽማግሌዎች ወይም ካህናት ሰዎቹ መእስኪገባቸው ድረስ ስለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንዲያብራሩላቸው ብቁ ጊዜን ማግኘት አለባቸው፣ ይህም ሁሉም ነገሮች በዕቅድ ይደረጉ ዘንድ ነው።
፷፱ እናም አባላቶቿ በቤተክርስቲያኗ ፊት እናም በሽማግሌዎች ፊት በአምላካዊ አካሄድ እና ንግግር ብቁ መሆናቸውን ያሳዩ፣ በጌታ ፊት ሀበቅድስና በመሄድ ከቅዱስ መፅሀፍቶች ጋር የሚጣጣሙ ለስራዎች እና እምነት ይኑራቸው።
፸ ልጆች ያሏቸው እያንዳንዱ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትም ልጆቻቸውን በቤተክርስቲያኗ ፊት ወደ ሽማግሌዎች ያምጡ፣ እነርሱም እጆቻቸውን በክርስቶስ ስም ልጆቹ ላይ ይጫኑ፣ እናም በእርሱ ስም ሀይባርኳቸው።
፸፩ ሀበተጠያቂነት እድሜ ላይ ካልደረሰ፣ እናም ለንስሀ ለመግባት ችሎታ ከሌለው፣ ማንም ሰው በክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን አይችልም።
፸፪ ንስሀ ለገቡት ሀጥምቀት ከእዚህ በሚከተለው ስነስርዓት ሁኔታ መሰጠት አለበት፥
፸፫ በእግዚአብሔር ተጠርቶ ለማጥመቅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ያለው ሰው፣ እራሱን ወይም እራሷን ለጥምቀት ካቀረበው ወይም ካቀረበች ሰው ጋር ወደ ውሀው አብሮ ይገባል፣ እናም እርሱን ወይም እርሷን በስም በመጥራት ይህን ይላል፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት፣ በአብ፣ በወልድ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቅሀለሁ (አጠምቅሻለሁ)። አሜን።
፸፬ ከዚያም እርሱን ወይም እርሷን ውሀ ውስጥ ሀያጥልቅ፣ እና ከውሀ ውስጥም በድጋሚ ያውጣ።
፸፭ ቤተክርስቲያኑም ዘወትር በአንድነት በመገናኘት ጌታ ኢየሱስን ሀማስታወስ ዳቦና ወይንን ለመካፈላቸው አስፈላጊ ነው፤
፸፮ እናም ሽማግሌ ወይም ካህን ይህንንም ያድርግ፤ እና በዚህ ሀመንገድም ይህን ያደርጋል—ከቤተክርስቲያኑ ጋር ተንበርክኮና በተረጋጋ ጸሎት ይህን በማለት አብን ይጥራ፥
፸፯ አቤቱ ዘለአለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ሀዳቦ ለሚቋደሱት ነፍሳት ሁሉ የልጅህን አካል በማሰብ እንዲበሉት እና፣ አቤቱ ዘለአለማዊ አባት እግዚብሔር ሆይ፣ እነርሱ የልጅህን ስም በላያቸው ላይ ለለመውሰድ ፈቃደኞች መሆናቸውን፣ እና ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱና እርሱ የሰጣቸውን ትእዛዛት ሐእንደሚጠብቁ ለአንተም መይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ ሠመንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሀለን። አሜን።
፸፰ ወይኑን የሚያስተላልፉበት ሀመንገድም ይህ ነው—ለኩባያውን ወስዶ እንዲህ ይላል፥
፸፱ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ሀወይን የሚጠጡት ነፍሳት ሁሉ ለእነርሱ የፈሰሰውን የልጅህን ደም በማስታወስ ያደርጉት ዘንድ፣ ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱ ለአንተም፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው፣ ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሀለን። አሜን።
፹ በኃጢአት የሚወድቅ ወይም በጥፋት የሚወሰዱ ማንም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል፣ ቅዱሳት መጻሀፍቱ እንደሚመሩት ይቀጣሉ።
፹፩ አንድ ወይም ብዙ መምህራንን በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ወደሚደረገው ብዙ ጉባኤዎች ላይ እንዲገኙ መላክም የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ክፍል የሆኑ ቤተክርስቲያናት ሀላፊነትም ነው፣
፹፪ በየወቅቱ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሀስም ዝርዝር ሌሎች ሽማግሌዎች በየጊዜው በሚሾሟቸው በአንዱ ሽማግሌ በመዝገብ ይጠበቅ ዘንድ ሲመጡም ካለፈው ጉባኤ በኋላ ራሳቸውን የቤተክርስቲያኗ አባላት ጋር አንድ ያደረጉትን ሰዎች ስም ይዘው ይምጡ፤ ወይም በአንዳንድ ካህናት እጅም ይላኩ፤
፹፫ ደግሞም፣ ማናቸውም ከቤተክርስቲያኑ ሀእንዲወጡ ቢደረጉም፣ ስማቸው ከቤተክርስቲያኑ ስም ዝርዝር ውስጥ እንዲሰረዙ ለማድረግ ነው።
፹፬ ወደ ማይታወቁበት ስፍራ አባላት ከሚኖሩበት ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲሄዱም፣ ጥሩ የቤተክርስቲያን አባል እንደሆኑ የሚዘረዝር የምስክር ወረቀት በደብዳቤ ይዘው መሄድ ይችላሉ፣ ይህ የምስክር ወረቀት ደብዳቤውን የሚወስደው ሰው ከሽማግሌው ወይም ከካህኑ ጋር የሚተዋወቅ ከሆነ፣ ማንኛውም ሽማግሌ ወይም ካህን ሊፈርም ይችላል፣ ወይም ይህም በመምህራን ወይም በዲያቆናት መፈረም ይችላል።