ክፍል ፹፬
በመስከረም ፳፪ እና ፳፫፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በመስከረም ወር ውስጥ፣ ሽማግሌዎች ከምስራቅ ስቴቶች ተልዕኮአቸው መመለስ እናም የአገልግሎታቸውን ሀተታ ማቅረብ ጀምረው ነበር። በዚህ የደስታ ዘመን ውስጥ አብረው እያሉ ነው ይህ መልእክት የመጣው። ነቢዩ ይህንንም የክህነት ራዕይ በማለት ሰይሞታል።
፩–፭፣ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም እና ቤተመቅደሱ በሚዙሪ ውስጥ ይገነባሉ፤ ፮–፲፯፣ የክህነት ዘር ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ተሰጥቷል፤ ፲፰–፳፭፣ ታላቁ ክህነት የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፍ ይዟል፤ ፳፮–፴፪፣ አነስተኛው ክህነት የመላእክትን አገልግሎት እና የማዘጋጃውን ወንጌል ቁልፍ ይዟል፤ ፴፫–፵፬፣ ሰዎች ዘለአለማዊ ህይወትን የሚያገኙት በክህነት ስልጣን መሀላ እና ቃል ኪዳን በኩል ነው፤ ፵፭–፶፫፣ የክርስቶስ መንፈስ ለሰዎች ያበራላቸዋል፣ እናም አለም በኃጢአት ተይዟል፤ ፶፬–፷፩፣ ቅዱሳን ስለተቀበሉት ነገሮች መመስከር አለባቸው፤ ፷፪–፸፮፣ እነርሱም ወንጌሉን ይስበኩ፣ ምልክቶችም ይከተላሉ፤ ፸፯–፺፩፣ ሽማግሌዎች ካለ ኮረጆም ወይም ከረጢት ይሂዱ፣ እናም ጌታ ለፍላጎታቸው ይንከባከባቸዋል፤ ፺፪–፺፯፣ ወንጌልን የሚቃወሙ ወረርሽኝ እና እርግማን ይጠብቃቸዋል፤ ፺፰–፻፪፣ ስለ ፅዮን መዳን የሚዘመረው አዲስ መዝሙር ተሰጥቷል፤ ፻፫–፻፲፣ እያንዳንዱም ሰው በሀላፊነቱ ይቁም እናም በጥሪውም ያገልግል፤ ፻፲፩–፻፳፣ የጌታ አገልጋዮች የመጨረሻ ቀናት የጥፋት ርኵሰትን ያውጁ።
፩ ለአገልጋዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ እና ለስድስት ሽማግሌዎች፣ በልባቸው አንድ ሲሆኑ እና ድምጻቸውን ወደላይ ሀከፍ ሲያደርጉ የተሰጠ የኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ።
፪ አዎን፣ ሀበነብያቱ አንደበት እንደተናገረው፣ ለህዝቦቹ ለዳግም መመለስ፣ እናም ሐአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከተማ በምትሆነው፣ መበፅዮን ተራራ በመቆም ሠለቅዱሳኑ መሰብሰቢያ እንድትሆን በመጨረሻዎቹ ቀናት የተመሰረተችውን ቤተክርስቲያን በተመለከተ ጌታ የተናገረው ቃል።
፫ ያም ከተማ፣ በጌታ ጣት በሚዙሪ ስቴት ምዕራፍ ድንበር ውስጥ በተመደበው፣ እና በጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ጌታ በተደሰተባቸው እጅ በተመረቀው፣ ሀበቤተመቅደስ ቅንጣት ምድር ተጀምሮ ይገነባል።
፬ እውነት ይህ የጌታ ቃል ነው፣ ሀየአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ከተማ በሚሰበሰቡት ቅዱሳን፣ በዚህ ስፍራ፣ እንዲሁም ለበቤተመቅደስ ስፍራ ተጀምራ ትገነባለች፣ ይህም ቤተመቅደስ በዚህ ትውልድ ይሰራል።
፭ በእውነትም ለጌታ ቤት እስከሚገነባ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍምና፣ እናም ደመናም ያርፍበታል፣ ደመናውም ቤቱን የሚሞላው የጌታ ሀክብር ይሆናል።
፮ እናም የሙሴ ልጆች፣ በአማቱ ሀበዮቶር ለእጆች በኩል በተቀበለው ቅዱስ ክህነት፤
፯ እናም ዮቶር በካሌብ እጅ ይህን ተቀበለ፤
፰ እና ካሌብም ይህን ከኢሊዮ እጅ ተቀበለ፤
፱ ኢሊዮ ይህን ከጀርሚ እጅ ተቀበለ፤
፲ እናም ጀርሚም ይህን ከጋድ እጅ ተቀበለ፤
፲፩ እና ጋድም ከኢሳይያስ እጅ፤
፲፪ እናም ኢሳይያስም ይህን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበለ።
፲፫ ኢሳይያስም በአብርሐም ቀናት ኖረ፣ እናም በእርሱም ተባርኮ ነበር—
፲፬ ይህም ሀአብርሐም ክህነትን፣ እስከ ለኖሀ ድረስ ከነበሩት ከአባቶቹ ዘሮች በተቀበለው ሐከመልከ ጼዴቅ ተቀበለ፤
፲፭ እናም ከኖህ እስከ ሀሄኖክ፣ በአባቶቻቸው ዘር በኩል ተቀበሉ፤
፲፮ እናም ከሄኖክም በወንድሙ ሀሽመቃ ምክንያት ወደተገደለው፣ በእግዚአብሔር ትእዛዛት ምክንያት የመጀመሪያው ሰው በነበረው በአባቱ ለአዳም እጅ ክህነትን ሐወደተቀበለው መአቤል—
፲፯ ይህም ሀክህነት በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በሁሉም ትውልዶች የሚቀጥል፣ እና ለቀናቱ መጀመሪያ ወይም ለአመታቱ መጨረሻ አመታት የሌለው ነው።
፲፰ እናም ጌታ ሀክህነትን ለበአሮን እና በዘሮቹ ላይ፣ በሁሉም ትውልዶች ውስጥ፣ አረጋገጠ፣ ይህም ክህነት ደግሞም ይቀጥላል እናም በቅዱሱ የእግዚአብሔር ስርዓት በኩል የሆነው ክህነት ለዘለአለምም ሐይቀጥላል።
፲፱ እናም ይህም ታላቅ ክህነት ወንጌሉን ያስተዳድራል እናም የመንግስቱን ሀሚስጥር ቁልፎች፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ለእውቀት ቁልፎችን፣ ይዟል።
፳ ስለዚህ፣ በዚህም ሀስርዓት ውስጥ፣ የአምላክ አይነት ሀይል ይታያል።
፳፩ ካለዚህም ስርዓት፣ እናም ካለክህነት ሀስልጣን፣ የአምላክነት ሀይል ለሰዎች በስጋ አይታይም።
፳፪ ካለዚህ ማንም ሀሰው የእግዚአብሔርን ፊት፣ እንዲሁም አብን፣ ለመመልከት እና ለመኖር አይችልም።
፳፫ አሁን ሀሙሴ በምድረበዳ ይህን ለእስራኤል ልጆች በግልፅ አስተማረ፣ እናም የእግዚአብሔርን ፊት ለይመለከቱ ዘንድ እንዲችሉም ህዝቦቹን ሐለመቀደስ በትህትና ፈለገ፤
፳፬ ነገር ግን፣ ልቦቻቸውን ሀአደነደኑ እናም በእርሱም ፊት ለመፅናት አልቻሉም፤ ስለዚህ፣ ጌታ ለበቁጣው፣ ንዴቱ በእነርሱ ላይ ስለተቀጣጠለ፣ በምድረበዳ ሳሉ ሁሉ ክብሩ ወደሆነው እረፍቱ ሐአይገቡም ብሎ መሀላ ገባ።
፳፭ ስለዚህ፣ ሀሙሴን፣ እናም ደግሞም ቅዱስ ለክህነትን ከመካከላቸው ወሰደ፤
፳፮ እናም የመላእክትን ሀአገልግሎት ለቁልፍን እና የመዘጋጃ ወንጌሉን የያዘው፣ አነስተኛው ሐክህነትም ቀጠለ።
፳፯ ይህም ወንጌል፣ ጌታ በቁጣው በአሮን ቤት በእስራኤል ልጆች መካከል ከእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ሀእስከተሞላው፣ እግዚአብሔር እስካነሳው ለዮሐንስ ድረስ እንዲቀጥል ያደረገው ሐየንስሀ እና መየጥምቀት፣ እና ሠየኃጢአት ስርየት፣ እና ረየስጋዊ ትእዛዛት ሰህግ ወንጌል ነው።
፳፰ በልጅነቱም ሳለ ነበር የተጠመቀው፣ እናም በስምንት ቀን እድሜውም፣ የአይሁድን መንግስት ለመጣል፣ እና በእጆቹ ሀሁሉም ሀይል ለተሰጠው ጌታ መምጫ ያዘጋጀው እና በህዝቦቹም ፊት የጌታን መንገድ ለያቀና ዘንድ ወደዚህ ሀይል በእግዚአብሔር መልአክ ተሹሞ ነበር።
፳፱ እና ደግሞም፣ የሽማግሌ እና የኤጲስ ቆጶስ ሀላፊነትም ከታላቁ ክህነት ጋር አስፈላጊ ሆኖ ሀየተያያዘ ነው።
፴ እና ደግሞም፣ የመምህር እና የዲያቆን ሀላፊነትም፣ በአሮን እና በልጆቹ ላይ ከተረጋገጠው፣ ከአነስተኛው ክህነት ጋር አስፈላጊ ሆነው የተያያዙ ናቸው።
፴፩ ስለዚህ፣ የሙሴን ልጆች በተመለከተ እንዳልኩትም—የሙሴ ልጆች እና ደግሞም የአሮን ልጆች ተቀባይ የሆነውን የሚቃጠል ሀመሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን በጌታ ቤት ውስጥ፣ በዚህ ትውልድ ለጌታ በተቀደሰው ለስፍራ እንደመደብኩት በሚገነባው ቤት፣ ያቀርባሉ—
፴፪ እናም የሙሴ እና የአሮን ወንድ ልጆችም፣ እነርሱም እናንተ ናችሁ፣ ሀበፅዮን ተራራ ላይ በጌታ ቤት ውስጥ በጌታ ለክብር ይሞላሉ፤ እና ደግሞም የጠራኋቸውና ሐቤተክርስቲያኔን እንዲገነቡ የላኳቸውም የእነርሱ ልጆች ናቸው።
፴፫ እነዚህን የተናገርኩባቸውን ሁለት ሀክህነቶች በማግኘት እና ጥሪያቸውን ለማጉላት ለታማኝ የሆኑት፣ ሰውነታቸውን በማደስ በመንፈስ ሐይቀደሳሉና።
፴፬ እነርሱም የሙሴ እና የአሮን ወንድ ልጆች፣ እናም ሀየአብርሐም ለዘር፣ እና ቤተክርስቲያንና መንግስት፣ እናም በእግዚአብሔር ሐየተመረጡ ይሆናሉ።
፴፭ እና ደግሞም ይህን ክህነት የሚቀበሉትም ሁሉ እኔን ይቀበሉኛል፣ ይላል ጌታ፤
፴፮ አገልጋዮቼን የሚቀበል እኔን ሀይቀበለኛልና፤
፴፯ እናም እኔን የሚቀበለኝም አባቴን ሀይቀበላል፤
፴፰ እናም አባቴን የሚቀበልም የአባቴን መንግስት ይቀበላል፤ ስለዚህ አባቴ ያለው ሀሁሉ ለእርሱም ይሰጠዋል።
፴፱ እናም ይህም በክህነት ባለ ሀመሀላ እና ቃል ኪዳን መሰረት ነው።
፵ ስለዚህ፣ ይህን ክህነት የሚቀበሉም፣ ሊሰበር የማይችለውን፣ ወይም ሊጠፋ የማይቻለውን፣ ይህን መሀላ እና ቃል ኪዳን ከአባቴ ዘንድ ይቀበላሉ።
፵፩ ነገር ግን ከተቀበለው በኋላ ይህን ቃል ኪዳን ሀየሚሰብረው፣ እና ከዚህም ሁሉ የሚዞርም፣ በዚህ አለምም ሆነ በሚመጣው አለም ለኃጢአቱ ምህረት ለአያገኝም።
፵፪ እናም እናንተ ወደተቀበላችሁት፣ በዚህ ቀን ለምትገኙትም ከሰማያት በራሴ ድምፅ ወዳረጋገጥሁላችሁ ክህነት ለማይመጡም ወዮላቸው፤ እናም የሰማይ ሰራዊትን እና ሀመላእክቴን እናንተን በሚመለከት ሀላፊነት ሰጥቻቸዋለሁ።
፵፫ እና አሁንም ራሳችሁን በተመለከተ እንድትጠነቀቁም፣ ለዘለአለም ህይወት ቃላትም በትጋት ሀታደምጡ ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፵፬ ከእግዚአብሔር አንደበት ከሚመጣው እያንዳንዱ ቃልም ሀትኖራላችሁና።
፵፭ የጌታ ሀቃል እውነት ነውና፣ እናም ለእውነት የሆነውም ብርሀን ነው፣ እናም ብርሀን የሆነውም መንፈስ፣ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ነው።
፵፮ እናም መንፈስም ወደአለም ለሚመጣው ሀለእያንዳንዱ ሰው ለብርሀን ይሰጣል፤ እናም መንፈስም በአለም ውስጥ ያለውን የመንፈስን ድምፅ ለሚያደምጥ ሰው ሁሉ ያበራለታል።
፵፯ እናም የመንፈስን ድምፅ የሚያደምጠው እያንዳንዱም ሰው ወደ እግዚአብሔር፣ እንዲሁም ወደአብ፣ ይመጣል።
፵፰ እናም አብም ያደሰውን እና በእናንተ ያረጋገጠውን ሀቃል ኪዳን ለያስተምረዋል፣ ይህንንም ያረጋገጠው ለእናንተ ጥቅም ነው፣ እናም ለእናንተ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ለአለም ሁሉ ጥቅም ነው።
፵፱ እና ሀአለምም ሁሉ በኃጢአት ተይዟል፣ እናም ለበጭለማ እና በኃጢአት ባርነት ስር ያቃስታል።
፶ እናም በዚህም ሀበኃጢአት ለባርነት ስር እንደሆኑም ታውቃላችሁ፣ ምክንያቱም ወደእኔ አይመጡምና።
፶፩ ወደእኔ የማይመጣው በኃጢአት ባርነት ስር ነውና።
፶፪ እናም ድምጼን የማይቀበልም ሀከድምጼ ጋር የተዋወቀ አይደለም፣ እናም ከእኔ አይደለም።
፶፫ እናም በዚህም ጻድቃንን ከኃጥአን ትለያላችሁ፣ እናም አሁንም ሀአለም ሁሉ ለበኃጢአት እና ጭለማ ስር ሐእንደሚያቃስቱ ታውቃላችሁ።
፶፬ እናም ባለፉት ጊዜያት አዕምሮአችሁ ሀባለማመን ምክንያት ጨልሞባችሁ ነበር፣ እናም የተቀበላችሁትን እንደተራ ተቀበላችሁታልና—
፶፭ ሀክንቱነት እና ያለማመን መላዋን ቤተክርስቲያን በፍርድ ላይ አድርገዋል።
፶፮ እናም ይህም ፍርድ በፅዮን ልጆች፣ እንዲሁም በሁሉም ላይ ያርፋል።
፶፯ እና እነርሱም ንስሀ እስኪገቡ እና አዲሱን ሀቃል ኪዳን፣ እንዲሁም ለመፅሐፈ ሞርሞንን እና የሰጠኋቸውን ሐየወደፊት ትእዛዛትን፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በጻፍኳቸው መሰረት መበማድረግ እስከሚያስታውሱ ድረስ ከዚህ ፍርድ በታች ይቆያሉ—
፶፰ ይህንንም የሚያስታውሱት ለአባታቸው መንግስትም የሚገባ ፍሬ ያመጡ ዘንድ ነው፤ አለበለዚያም መቅሰፍት እና ፍርድ በፅዮን ልጆች ላይ ይወርድባቸዋል።
፶፱ የመንግስት ልጆች ቅዱስ ምድሬን ይበክላሉን? በእውነት፣ እላችኋለሁ፣ አይበክሉም።
፷ በእውነትም፣ ድምጼ የሆናችሁ እናንተ፣ ሀቃላቴን አሁን ለምትሰሙ ይህን እላችኋለሁ፣ እነዚህን ነገሮች እስከተቀበላችሁ ድረስ የተባረካችሁ ናችሁ፤
፷፩ በአእምሮአችሁ ሀበእርጋታ እና በጸሎት መንፈስ፣ በመሆን የሰማችሁትንም እነዚያን ነገሮች ለአለም ትመሰክሩ ዘንድ—በዚህ ትእዛዝ ኃጢአታችሁን ለይቅር እላለሁና።
፷፪ ስለዚህ፣ ወደ አለም ሁሉ ሀሂዱ፤ እናም ልትሄዱ በማትችሉበትም ቦታ፣ ከእናንተ ምስክራችሁ ወደ አለም ሁሉ ወደ እያንዳንዱ ፍጥረት እንዲሄድ፣ ላኩ።
፷፫ እናም ሀለሐዋሪያቴ እንዳልኳቸውም፣ ለእናንተም እላለሁ፣ ለእናንተም ይህን ሐዋሪያቴ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ናችሁ፤ እናንተም አባቴ ለየሰጠኝ ናችሁ፤ ሐጓደኛዎቼም ናቸሁ፤
፷፬ ስለዚህ፣ ለሐዋሪያቴም እንዳልኳቸው ለእናንተም ደግሜ እላለሁ፣ በቃላቶቻችሁ ሀየሚያምኑት እናም ኃጢአታቸው ለይሰረይ ዘንድ በውሀ የሚጠመቁ እያንዳንዱ ሐነፍሳትም መመንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ።
፷፭ እናም ያመኑትንም እነዚህ ሀምልክቶች ይከተሉአቸዋል—
፷፮ በስሜም ብዙ ድንቅ ሀስራዎች ይሰራሉ፤
፷፯ ሀበስሜም አጋንንትን ያወጣሉ፤
፷፰ በስሜም የታመሙትን ሀይፈውሳሉ፤
፷፱ በስሜም የእውሩን አይኖች ያበራሉ፣ እናም የደንቆሮዎችን ጆሮዎች ይከፍታሉ፤
፸ እናም የዲዳውም ምላስ ይናገራል፤
፸፩ እናም ማንም ሰው ሀመርዝ ቢሰጣቸውም አይጎዳቸውም፤
፸፪ እናም የእባብ መርዝም ሊጎዳቸው በእነርሱ ላይ ሀይል አይኖረውም።
፸፫ ነገር ግን፣ በእነዚህ በሚሆኑነገሮች በራሳቸው ሀእንዳይታበዩ፣ ወይም በአለም ፊትም እንዳይናገሩ ትእዛዝ እሰጣቸዋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ጥቅም እና ደህንነት ተሰጥተዋልና።
፸፬ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በቃላቶቻችሁ የማያምኑት፣ እናም መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ በስሜ በውሀ ውስጥ ለኃጢአታቸው ስርየት ሀያልተጠመቁት፣ ለይፈረድባቸዋል፣ እናም እኔ እና አባቴ ወዳለንበት ወደአባቴ መንግስትም አይመጡም።
፸፭ እናም ለእናንተ የተሰጠው ይህ ራዕይ እና ትእዛዝ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በአለም ሁሉ ላይ የሚሰራ ነው፣ እናም ወንጌሉም ላልተቀበሉት ሁሉም ነው።
፸፮ ነገር ግን፣ መንግስት ለተሰጣቸው ሁሉ በእውነት እላለሁ—ለቀደመው ክፉ ስራቸው ንስሀ ይገቡ ዘንድ፣ ለክፉና ለማያምን ልቦቻቸውም፣ እናም በላኳችሁ ጊዜ ያመጹት በፅዮን ያሉት ወንድሞቻችሁም ይነቀፋ ዘንድ ይህም ከእናንተ ለእነርሱ መሰበክ ይገባል።
፸፯ እና ባልንጀሮቼ፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ባልንጀሮቼ ብዬ እጠራችኋለሁና፣ ደግሜም እላችኋለሁ፣ ከእነርሱ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ወንጌልን ለመስበክ በሀይሌ በሚጓዙበት ቀናት እንደነበሩት ባልንጀሮቼ ትሆኑ ዘንድ ይህን ትእዛዝ ለእናንተ መስጠቴ አስፈላጊ ነው፤
፸፰ ሁለት እጀ ጠባብም ይሁን ሀኮረጆም ወይም ከረጢት እንዲኖራቸው አልፈቀድኩላቸውምና።
፸፱ እነሆ፣ አለምን ትፈትኑ ዘንድ ልኬአችኋለሁ፣ እና ለሠራተኛም ሀደመወዙ ይገባዋል።
፹ እናም ማንም የሚሄድና ይህን የመንግስትን ሀወንጌል ለየሚሰብክ፣ እናም በሁሉም ነገሮች በእምነቱ ጸንቶ የቆመ ሰው፣ በአዕምሮ ወይም በሰውነት፣ በእግርና እጆቹ፣ ወይም መገጣጠሚያዎቹ አይደክሙም ወይም አይዝሉም፤ እናም የራሱም ሐጠጉር ሳይታወቅ ምድር ላይ አይወድቅም። እናም አይራቡም ወይም አይጠሙም።
፹፩ ስለዚህ፣ ለነገ ምን እንደምትበሉ፣ ምን እንደምትጠጡ፣ ወይም ምን እንደምትለብሱ ሀአትጨነቁ።
፹፪ የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ እናም የዓለም መንግሥታት እንኳ በክብራቸው ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሱም።
፹፫ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ ሀአባታችሁ ለያውቃልና።
፹፬ ስለዚህ፣ ነገ ለራሱ ሀይጨነቅ።
፹፭ እንዴት ወይስ ሀምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ ነገር ግን ዘወትር የህይወትን ቃል በአዕምሮዎቻችሁ ውስጥ ለአከማቹ፣ እና ይህም በዚያች ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰው ተመዝኖ የሚሰጠው ሐይሰጣችኋል።
፹፮ ስለዚህ፣ ይህ ትእዛዝ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ለአገልግሎት በእግዚአብሔር ለተጠሩት ሀታማኝ ለሆኑት ሁሉ ስለሆነ፣ የመንግስትን ወንጌል ለማወጅ የሚሄድ ማንም ሰው ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ኮረጆም ወይም ከረጢት አይውሰድ።
፹፯ እነሆ፣ ጻድቅ ላልሆነው ስራዎቻቸው ዓለምን እንድትወቅሱ፣ እና ስለሚመጣው ፍርድም ታስተምሯቸው ዘንድ ሀልኬአችኋለሁ።
፹፰ እናም ሀየሚቀበሏችሁም ቢሆን፣ እኔም በዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁም እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልባችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም ይደግፏቹም ዘንድ ለመላእክቴ በዙሪያችሁ ይሆናሉ።
፹፱ ማንም የሚቀበላችሁ እኔን ይቀበለኛል፤ እናም እርሱም ይመግባችኋል፣ እናም ያለብሳችኋል፣ እናም ገንዘብም ይሰጣችኋል።
፺ እናም የሚመግባችሁ፣ ወይም የምሚያለብሳችሁ፣ ወይም ገንዘብንም የሚሰጣችሁ፣ በምንም ዋጋው ሀአይጠፋበትም።
፺፩ እናም እነዚህን ነገሮች የማያደርገው እርሱ ደቀ መዛሙርቴ አይደለም፤ በዚህም ሀደቀመዛሙርቴን ታውቋቸዋላችሁ።
፺፪ ለማይቀበላችሁም፣ ከእርሱ ተለይታችሁ ውጡ፣ እናም በሙቀትም ይሁን በቅዝቀዛ እግሮቻችሁን በውሀ፣ እንዲሁም በንጹ ውሀ ሀአጽዱ፣ እናም ምስክርንም ለሰማይ አባታችሁ አቅርቡ፣ እናም ወደእርሱም ደግማችሁ አትመለሱ።
፺፫ እናም በምትገቡበትም መንደር ወይም ከተማ፣ ይህንኑ አድርጉ።
፺፬ ይህም ቢሆን፣ ተግታችሁ ፈልጉ እናም አትታክቱ፤ እናም እናንተን ወይም ቃላቶቻችሁን፣ ወይም እኔን በመመልከት ያላችሁን ምስክር ለማይቀበል ለዚያ ቤት ወይም መንደር ወይም ከተማ ወዮለት።
፺፭ እናንተን ወይም ቃላቶቻችሁን፣ ወይም እኔን በመመልከት ያላችሁን ምስክር ለማይቀበል ለእዚም ቤት ወይም መንደር ወይም ከተማ ደግሜ ወዮለት እላለሁ።
፺፮ እኔ፣ ሀሁሉን የሚገዛው፣ ለጥፋተኝነታቸውን ሐለመቅጣት እጆቼን በአህዛብ ላይ አሳርፌአለሁ።
፺፯ እናም መቅሰፍቶችም ይሆናሉ፣ እናም ስራዬን እስከምጨርስ ድረስም አይወሰዱም፣ ይህም በፅድቅ ሀበአጭር ይቆረጣል—
፺፰ የሚቀሩት፣ እንዲሁም ከታናሹ ጀምሮ እስከታላቁ፣ ሁሉ እስከሚያውቁኝ ድረስ፣ እናም በጌታ እውቀትም ይሞላሉ፣ እናም ሀዓይን ለዓይን ይተያያሉ፣ እናም ድምፃቸውንም ያነሣሉ፥ እናም በአንድነትም ይህን አዲስ መዝሙር እንዲህ በማለት ለይዘምራሉ፥
፺፱ ጌታ ፅዮንን ዳግም መልሷል፤ጌታ ሕዝቡ፣ ሀእስራኤልን፣ ለአድኗል፣ሐበጸጋ በሆነ መምርጫ፣እናም በአባቶቻቸው ሠቃል ኪዳን፣ይህም በእምነት የተከናወነ ነበር።
፻ ጌታ ህዝቡን ተቤዠእናም ሰይጣንም ሀታስሯል እና የጊዜ ቀመር አይኖርም።ጌታ ሁሉንም ነገሮች ለበአንድ ጠቅልሏል።ጌታ ሐፅዮንን ከላይ መልሶ አምጥቷል።ጌታ ፅዮንንም ከታችም መልሶ መአምጥቷል።
፻፩ ሀምድርም አምጣለች እና ጥንካሬዋንም አምጥታለች፤እውነትም በሆዷ ውስጥ የተመሰረተ ነው፤እና ሰማያትም በእርሷ ላይ ፈገግ ይላሉ፤እናም እርሷም የአምላኳን ለክብር ልብስ ለብሳለች፤እርሱም በሕዝቦቹ መካከል ቆሟልና።
፻፪ ክብር፣ እና ሀይል፣ እና ብርታት፣ለአምላካችን ይሁን፤ እርሱም ሀበምህረት፣በፍትህ፣ በጸጋ፣ እና ለበሰላም የተሞላ ነውና፣ከዘለአለም እስከዘለአለም፣ አሜን።
፻፫ እና ደግሞም፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ዘለአለማዊ ወንጌሌን ለማወጅ የሚሄደው እያንዳንዱ ሰው፣ ቤተሰብ ያላቸው ቢሆን፣ እናም የገንዘብ ስጦታን ቢቀበሉ፣ ይህን ጌታ እንደሚመራቸው ለእነርሱ እንዲልኩ ወይም ለእነርሱ ጥቅም ያውሉት ዘንድ አስፈላጊ ነው፣ ይህም መልካም ነውና።
፻፬ እናም ሀገንዘብ የሚቀበሉት ቤተሰብ የሌላቸውም፣ ለራዕዮች መገለጥ እና መታተም እናም ለፅዮን መመስረት የተቀደሰ ይሆን ዘንድ፣ ወደ በፅዮን ወይም በኦሀዮ ላለ ኤጲስ ቆጶስ ይላኩት።
፻፭ እናም ማንም ሰው ኮት ወይም ሙሉ ልብስን ቢሰጣችሁ፣ አሮጌውን ወስዳችሁ ሀለደሀው ስጡ፣ እናም በደስታም ሂዱ።
፻፮ እናም በመካከላችሁ አንዱ ሰው በመንፈሱ ጠንካራ ቢሆን፣ ሀበቅንነት እንዲታነጽ፣ ደግሞም ጠንካራ ይሆን ዘንድ፣ ከእርሱ ጋር ደካማ የሆነውን ለይውሰድ።
፻፯ ስለዚህ፣ ከእናንተ ጋር ሀበአነስተኛው ክህነት የተሾሙትን ውሰዱ፣ እናም ቀጠሮም ያድርጉ፣ እናም መንገድንም እንዲያዘጋጁላችሁ፣ እናም እናንተ ራሳችሁ ልታከናውኑት የማትችሉትን ቀጠሮ ያሟሉላችሁ ዘንድ በፊታችሁ ስደዷቸው።
፻፰ እነሆ፣ ይህም በቀደሙት ጊዜያት ሐዋሪያቴ ቤተክርስቲያኔን የገነቡበት መንገድ ነው።
፻፱ ስለዚህ፣ እያንዳንዱ ሰው በተሾመበት ይቁም፣ እናም በጥሪውም ያገልግል፤ እናም ራስ ለእግር እግር አስፈላጊ አይደለም አይበለው፤ ምክንያቱም ያለእግር ሰውነት ሊቆም ይቻለዋል?
፻፲ ደግሞም፣ ሁሉም አብረው ይታነጹ ዘንድ፣ አሰራሩም በፍጹም ሆኖ ይቀጥል ዘንድ፣ አካል እያንዳንዱ ሀብልቶች ያስፈልጉታልና።
፻፲፩ እናም እነሆ፣ ሀሊቀ ካህናት፣ እና ደግሞም ሽማግሌዎች፣ እና ደግሞም አነስተኛዎቹ ለካህናት ይጓዙ ዘንድ ይገባል፤ ነገር ግን ሐዲያቆናት እና መመምህራን ቤተክርስቲያኗን ሠእንዲጠብቁ፣ በቤተክርስቲያኗ የማይጓዙ አገልጋዮች በመሆን እንዲወከሉ ይገባቸዋል።
፻፲፪ እናም ኤጲስ ቆጶሱ፣ ኒወል ኬ ውትኒ፣ ደግሞም በአካባቢው እና በቤተክርስቲያናቱ መካከልም፣ የደሆችን ፍላጎት በመጠበቅ ሀብታሞችን እና ትእቢተኞችን ሀዝቅ በማድረግ ለለመርዳት መጓዝ ይገባዋል።
፻፲፫ ሀላፊነትን እንዲወስድ እና በሚመራው መንገድ ስጋዊ ሀላፊነትን እንዲያከናውን ሀወኪልንም መጥራት ይገባዋል።
፻፲፬ ይህም ቢሆን፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወደ ኒው ዮርክ ከተማ፣ ደግሞም ወደ አልበኒ ከተማ፣ እናም ደግሞም ወደ ቦስተን ከተማ ይሂድ፣ እናም የእነዚህ ከተማ ሰዎችንም በወንጌሉ ድምጾች፣ በጎላ ድምፅ፣ እነዚህን ነገሮች ቢቃወሙ ስለሚጠብቃቸው ሀውድመት እና የከፋ ጥፋት ያስጠንቅቅ።
፻፲፭ እነዚህን ነገሮች ቢቃወሙ የፍርዳቸው ሰአት ደርሶአልና፣ እናም ቤታቸውም ሀበውድመት ይቀርላቸዋል።
፻፲፮ በእኔ ሀይመን እናም እርሱም ለአያፍርም፤ እናም የራሱም ሐጠጉር ሳይታወቅ ምድር ላይ አይወድቅም።
፻፲፯ እናም እውነት እላችኋለሁ፣ የቀራችሁት አገልጋዮቼ፣ ጉዳያችሁ እንደሚፈቅድላችሁ፣ በተለያዩት ጥሪዎቻችሁ፣ ወደታላቅ እና ታዋቂ ከተማዎች እና መንደሮች፣ በፅድቅ አለምን ጻድቅ ላልሆኑ እና እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ስራዎቻቸውን እየወቀሳችሁ፣ በግልፅ እና በሚገባ ሁኔታ የመጨረሻ ቀናት የጥፋት ርኩሰትን በመግለፅ ሂዱ።
፻፲፰ በእናንተም መንግስቶቻቸውን ሀእደመስሳቸዋለሁ፤ ምድርን ለማናውጥ ብቻ ሳይሆን፣ ኮከባዊውን ሰማያትንም አናውጣለሁ ይላል ሁሉን የሚገዛው አምላክ።
፻፲፱ እኔ ጌታ የሰማይን ሀይላት ለመጠቀም እጆቼን እዘረጋለሁና፤ አሁን ልታዩት አትችሉም፣ ነገር ግን ከትንሽ ጊዜ በኋላ ታዩታላችሁ፣ እናም እኔ እንደሆንኩኝ፣ እናም በህዝቤ መካከል ሀለመንገስ ለእንደምመጣም ታውቃላችሁ።
፻፳ እኔ ሀአልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው፣ ነኝ። አሜን።